የሕይወት ታሪክ

የታርጂያት ደቦል ሉል የሕይወት ታሪክ እኔ መምህር ታርጂያት ደቦል ሉል ከአባቴ ከአቶ ደቦል ሉል እና ከእናቴ ከወ/ሮ ማርታ ኛቦም ቧክ ግንቦት 08 ቀን 1982 ዓ.ም. በጋምቤላ ክልል፣ በኑዌር ዞን፣ ዋንቷር በተባለ አካባቢ ተወለድኩ። አድገቴ በገጠር እንደመሆኑ መጠን እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ የገጠር ልጅ በልጅነቴ ከብቶችንና ፍየሎችን በመጠበቅና በመንከባከብ አደኩ፣ ዕድሜዬ ለትምህርት ሲደርስም የመደበኛ ትምህርቴን በዳልኮች አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መከታተል ጀመርኩ። በመቀጠልም የሁለተኛ ደረጃና የመሰናዶ ትምህርቴን በጋምቤላ ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት በማጠናቀቅ የከፍተኛ ትምህርቴን በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመከታተል በ2005 ዓ.ም. የመጀመሪያ ዲግሪዬን (BA) በሶሺዮሎጂ (Sociology) አገኘሁ። የመጀመሪያ ዲግሪዬን እንዳጠናቀቅኩም በዚሁ በ2005 ዓ.ም. በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመምህርነት (Lecturer) ተቀጥሬ ወደ ሥራው ዓለም ተቀላቀልኩ። ሙያዊና አካዳሚያዊ ዕውቀቴን የበለጠ ለማሳደግ ባደረግኩት ጥረት በ2016 ዓ.ም. ከቱርክ ስታምቡል ኮሜርስ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ የማስተርስ ዲግሪዬን (1st MA) በዓለም አቀፍ ግንኙነት እና የአፍሪካ ጥናት (International Relations and African Studies) ያገኘሁ ሲሆን፣ ይህንኑ በማስቀጠል በኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ በስትራቴጂና ደህንነት ጥናት (Security and Strategic Studies) ተጨማሪ ሁለተኛ ዲግሪ (2nd MA) አግኝቻለሁ፣ የትምህርት ደረጃየን የበለጠ ለማሳደግ በማሰብ አሁን የዶክትሬት ዲግሪ (PhD) ትምህርቴን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰላም እና የደህንነት ጥናት ተቋም (IPSS) በሰላም እና ደህንነት ጥናት በቁርጠኝነት በመከታተል ላይ እገኛለሁ። ከሥራን ትምህርት ስራ ጎን ለጎን የቤተሰብ ሕይወትን በመሥራት በ2009 ዓ.ም. ትዳር የመሠረትኩ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት የሦስት ሴቶች ልጆች አባት ነኝ። በሥራ ዘመኔ በሙሉ ለአገሬና ለወገኔ ጠቃሚ የሆኑ በርካታ ተግባራትን ማለትም በመምህርነት፣ በፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች እንዲሁም በልዩ ልዩ የበጎ ፈቃደኝነት ሥራዎች ላይ በንቃት በመሳተፍ የበኩሌን አዎንታዊ አስተዋጽኦ አበርክቻለሁ። በአሁኑ ወቅትም በአዲስ አበባ በሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ መከላከያ ኮሌጅ (ቀደም ሲል የኢ.ዲ.ዲ.ሪ የመከላከያ ዋር ኮሌጅ በመባል ይታወቅ የነበረው) በመምህርነት እያገለገልኩ እገኛለሁ።