የሕይወት ታሪክ

ፈንታዉ አዋየሁ መለሰ ዜግነት ኢትዮጵያዊ ፆታ ወንድ e-mail fentawawayehu2025@gmail.com ስልክ 0902771595\0914716339 ባህርዳር|ኢትዮዽያ አጭር የስራ ልምድ  እኔ በተቋም አስተደደር ከ32 ዓመት በላይ የሠራው ሲሆን በተለያዩ የወረዳ፣ የዞንና የክልል ተቋማት በመስራቴ የተቛማትን ችግሮች በመለየትና ቅደም ተከተል በማውጣት፣ በማቀድ፣ በመከታተል፣ በመገምገም፣ በማቀናጀትና በመምራት ከፍተኛ ልምድ አለኝ፡፡  በተለያዩ ተቋማት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ሁኘ በመመደብ ህዝብን የማስተማርና በጥቅሙ ዙሪያ እንዲስበሰብ የማድረግ ሥራ በመሥራት ውጤታማ ስራ ሠርቻለሁ፡  ከወረዳ እስከ ክልል በሰራዉባቸዉ ተቛማት የሰው ኃይል ስምሪትን በማቀድ፣ በማሰማራት፣ በመከታተል፣ በማስተዳደርና በመደገፍ ቁልፍ የተግባር ፈፃሚ እንዲሆን በማድረግ የእረጅም ጊዜ ልምድ አለኝ::  የአካባቢ ጥበቃ ሥራ ለሃገር ያለውን ፋይዳ ህብረተሰቡ እንዲገነዘብና የአካባቢውን የተፈጥሮ ሃብት እንዲጠብቅ በተለይም ውሃማ አካላትንና ጥበቅ ደኖችን እንዲንከባከብ የሚያስችል ግንዛቤ እንዲፈጥር የማስተባበር  ህብረተሰብን በማነሳሳት ለልማት ሃብቱን፣ ጉልበቱንና እውቀቱን አስተባብሮ ት/ቤቶች፣ ጤና ኬላዎች እንዲገነቡና እንዲጠገኑ የተፈጥሮ ሃብት ሥራን እንዲሠራና እንዲንከባከብ በማስተማርና ቴክኖሎጂን በማስተዋወቅና እንዲላመድ በማድረግ ጥሩ ልምድ አግኝቻለሁ፡፡ (የሳሳካው ግሎባል 2000 ፕሮግራም)  የመሬትን ሃብት በአግባቡ አውቆ ለመምራት የሰሜን ወሎ ዞን አርሶ አደሮች የመጀመሪያ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር በተጣራ መንገድ እንዲሰነዱ በማድረግ ከ2 ዓመት በላይ በመምራት ልምድ አትርፊያለሁ፡፡  ከወረዳ እስከ ክልል በተለያዩ ሀላፊነቶች በሰራዉበት ዓመታት ለልማት የተበጀተ በጀት በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዲውል በማድረግ የመንግስት እቅድ በማሳካትና የህዝቡን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ከፍተኛ ልምድ አግኝቻለሁ፡፡  የአስተዳደርና ሎጀስቲክስ ዘርፍ ሃላፊ ሁኘ በምመራው ተቋም በአመት እስከ 2,000,0000,000 ብር የሚደርስ በጀት የሚንቀሳቀስበት 6 የመንገድ ግንባታና ጥገና ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች፣ 38 የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶችና በስራቸው እስከ 1765 የሚደረስ ሠራተኛን ጥቅም አስከብሮ የማንቀሳቅስ፣ በአማካይ ከ1.9 እስከ 2 ቢሊዮን ብር የሚያወጣ፣ የነዳጅ፣ የብረት፣ የስሚንቶ፣ የማሽንና ተሽከርካሪ ኪራይ አገልግሎት ግዥ በመፈፀም ከ600 የማያንስ ማሽንና ተሽከርካሪ ያለበትን ሁኔታ አውቆ እንዲጠገንና እንዲስማራ የማድረግ ከፍተኛ ልምድ አለኝ፡፡ • በተጨማሪም የቦርድ አባል በመሆን ከ2 አመት በላይ ስለሥራው ተቋማት ትርፋማ ለመሆን እንዴት ማቀድና መምራት እንዳለባቸው ተጨባጭ አቅም የሚሆን ልምድ አለኝ፡፡ የትምህርት ሁኔታ • የመጀመሪያ ዲግሪ /BSC/ በአደጋ መከላከልና ቀጣይ ልማት ከባህር ዳር ዩኒቨርስቲ በ2002 • ዲፕሎማ በስራ አመራር ከአልፋ ዩኒቨርስቲ 1997 ዓ.ም የሥራ ልምድ ሁኔታ ከ2012 መስከረም 1 እስካሁን ድረስ • በአማራ ገጠር መንገድ ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ በም/ስራ አስኪያጅ የአስተዳደር ዘርፍን ኃላፊነት የሆነውን ከ1765 በላይ የሠው ኃይል ጥቅሙን አስከብሮ የሥራ ኃላፊነቱን እንዲወጣ የመከታተልና መምራት በዓመት እስከ 2,500,000,000 (ሁለት ቢሊዮን አምስት መቶ ሚሊዮን) ብር የሚንቀሳቀስበት የፋይናንስ ክፍል በማስተባበር በአማካይ ከ1.9 እስከ 2 ቢሊዮን ብር ግዥ እንዲፈፀምና የተቋሙ ንብረት የሆነውን እስከ 600 የሚደርስ ማሽንና ተሽከርካሪ የጥገናና ስምሪት ስራ በመምራት ከፍተኛ የሥራ ልምድ አግኝቻለሁ፡፡ ከ2008 ህዳር 1 እስከ 2011 ጷግሜ 6 ድረስ በክልሉ መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ የዩራፕ ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ በመሆን በፕሮግራሙ ተጀምረዉ የነበሩ 2280 ኪ.ሜ መንገዶች እንዲገነቡ፣ ተዘለው የነበሩ1746 አነስተኛና ከፍተኛ ስትራክቸሮችና 39 ከፍተኛ ድልድዮች እንዲገነቡ በማድረግ የህብረተሰቡን የልማት ጥያቄ ለመመለስ ከፍተኛ ስራ ሰርቻለዉ፡፡በተለይ ደግሞ 2011 ላይ የክልሉ መንግስት በአስቀመጠዉ አቅጣጫ መሰረት ህብረትሰቡን በመንገድ ግንባታዉ ላይ ማሳተፍ አስፈላጊ መሆኑ ስለታመነበት 315,314,755 ብር በማሰባሰብ በራሱ አቅም መንገዶችን እንዲገነባ የማስተባበር ስራ ስረቻለሁ፡፡ በተመሳሳይ በስራቸው ውጤታማ ሳይሆኑ ቀርተው የተበተኑ በፕሮግራሙ የተደራጁ 28 ማህበራት አስቀድመዉ ከፍለዉት የነበር የሊዝ ክፍያ ብር 60,308,862 እንዲመለስላቸዉ በማድረግ ይጠቀሙባቸው የነበሩና በየቦታው ጥለዋቸው የተበታተኑትን 28 ተሽከርካሪዎችና የተለያዩ ቁሳቁሶች በማሰባሰብ በዞኖች እንዲተዳደሩ በማድረግ ከፍተኛ ሃብት ከብክነት እንዲድን የማድረግ ሥራ በመሥራት ጠንካራ ውሳኔ የሚፈልጉ ኃላፊነቶችን መወጣት ችያለሁ፡፡ ከ2003 ሰኔ እሰከ 2008 ጥቅምት 30 ድረስ በም/ቢሮ ኃላፊነት ደረጃ የኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ በመሆን • ከተሞች ለህዝብ መስጠት ያለባቸውን አገልግሎቶች አሟልተው እንዲሰጡ • በከተሞች የሚሰሩ የልማት ሥራዎች ለህዝቡ ያላቸውን ፋይዳ ግንዛቤ እንዲያዝበት በማድረግ • ኢንቨስትመንት የግል ባላሃብቱን ወደ ሥራ እንዲገባ ማድረግ ተኪ ምርት ከማምረት በተጨማሪ ሰፊ የሥራ እድል በመፍጠር በኩል ያለው ድረሻ በአግባቡ እንዲታወቅ • መሬት የኢኮኖሚ መሠረት የሆነ አላቂ ሃብት እንደሆነ ግምት በማስገባት የከተማ መሬትን በቁጠባና በተመረጠ አግባብ ጥቅም ላይ እንዲውል ግንዛቤ እንዲያዝበት ለመድረግ • ከተሞች ለነዋሪዎቻቸው የተሟላ አገልግሎት እንዲሰጡ አሰቀድሞ በፕላን እንዲመሩ ማድርግ ያለውን ፋይዳና መሠል ጉዳዬችን መሰርት በማድረግ በመድረክና በተለያዩ ህትመቶች የማስተዋወቅና የማስገንዘብ ሥራ በመስራት የማህብረሰቡን ግንዛቤ ማስተካከልና የአመላካከት ዝንፈትን በማረም ከፍተኛ ሥራ ሠርቻለሁ፡፡ ከ1999 ሚያዚያ እስከ 2003 ዓ.ም ድረስ በዞን የህዝብ ግንኙነት አማካሪነትና በመሬት አስተዳደርና አካባቢ ጥበቃ መምሪያ ኃላፊነት ሳገለግል ቆይቻለሁ፡፡ • ህብረተሰቡ በሁሉም ልማቶች ላይ የራሱን ድረሻ እንዲወጣ ግንዛቤ የመፍጠር የማስተባበር ሥራ በመስራት • በዞኑ አ/አደር የመሬት ባለቤትነት ደብተር የወሰዱበት አግባብ ላይ የነበረውን የግንዛቤ ጉድለት በመሙላት ህብረተሰቡ ጋር መተማመን በመድረስ በትርፋነት የተወሰዱ ከ4000 በላይ ደብተሮች እንዲመለሱና ሁሉም አ/አደር መሬቶቹ በአግባቡ ተዘርዝረውለት አንድ ደብተር እንዲይዝና የመሬት ባለቤትነቱን እንዲያሰከብር በማድረግ • በዞኑ ውስጥ ያሉ ጥበቅ መሬቶችና ዉሀማ በአካባቢዎች በአ/አደሩ እንዳይታረሱ ወይም እንዳይገፉ ጉዳቱን በማስተማርና መተማመን ላይ በማድረስ ነዋሪው አካባቢውን እንዲጠብቅ በማድረግ • ማንኛውም ወደ ኢንቨስትመንት የገባ አካል አስቀድሞ EIA የአካባቢ ተስማሚነት ፕላን እንዲያሰራና የሚደርሰውን አካባቢያዊ ተፅፅኖ እንዴት ማኔጅ ማድረግ እንዳለበት በማስገንዘብና የማህብረሰቡን ጥቅም እንዲከበር በማድረግ በርካታ ሥራዎች ሠርቻለሁ፡፡ከሥራዎቹ አፈፃፀም ከራሳቸው ከፍተኛ ልምድ አግኝቻለሁ፡፡ ከ1988 ታህሳስ እስከ 1999 መጋቢት በወረዳ አስተዳደሪነት፣ ም/አስተዳዳሪነትና በከተማ ም/ከንቲባነት ያገለገልኩ ሲሆን • ለህብረተሰቡ ልማት የሚበጀት በጀት በአግባቡ በመምራት የህዝቡን ተቀዳሚ ችግር በመፍታት ላይ የተመሠረተ ሥራ በመሥራት • የህዝቡን የማምረት አቅም ለማሳደግ አ/አደሩ የግብርና ግብዓት (ማዳበሪያ) እንዲጠበቅ በማስተማርና በማለማመድ ከፍተኛ ለውጥ እንዲመጣ በማድረግ • የነበረውን የትምህርትና የጤና ሽፋን ለማሳደግ በየገጠር ቀበሌዎቹ ት/ቤትና ጤና ኬላ እንዲገነባ የህዝቡን ጉልበትና ገንዘብ በማስተባበር ከፍተኛ ለውጥ እንዲወጣ የሚያደርግ ሥራ እንዲሠራ በመምራት • የማህብረሰቡ የኑሮ መሠረት የሆነው መሬት ለምነት እንዲጠበቅ በየዓመቱ ከፍተኛ ህዝብ በማስነሳት የአፈርና ውሃ እቀባ ሥራ እንዲስራ በማድረግ ውጤታማ የሆነ ስራ በመሥራት እንዲሰራ የማቀድና የማሰተባበር ሥራ በመሥራት • ማንኛውም ሠው በተለይ የከተማው ነጋዴ በሰራውና በተጠቀመው ልክ ግብር ካልከፈለ የከተማውን መሠረት ልማት ማሟላት እንዳማይቻል ተገንዝቦ ግብርን በወቅቱ እንደከፍል በማስተባበር ሰፊ ስራ የሠራው ሲሆን ከፍተኛ ልምድ አግኝቻለሁ፡፡