የሕይወት ታሪክ

ሙስሊማ ረሺድ እባላለው በ 1984 ከአባቴ ረሺድ አባግዲ እና ከእናቴ አምበሩ ሸህ መሐመድ በጅማ ዞን ልሙ ኮሳ ጫካዎ መንጂ በምትባል ቀበሌ ማህበር ዉስጥ ተወለድኩ. የአንደኛ ደረጃ ትምህርቴን ከ 1-6 ዎሌንሱ ትምህርት ቤት ተማርኩ. ከ 7-8 ልሙ ገነት አንደኛ ደረጃ እና ከ 9-10እዛው ልሙ ገነት ሁለትኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማርኩኝ. ከ 1999-2002 በመቱ መምህራን ኮሌጅ የመምህርነት ሞያን በድፕሎማ ተማርኩ. በ2002 ተመርቄ በመምህርነት ሞያ እስከ 2007 በልሙ ኮሳ ወረዳ ውስጥ የተለያዩ ትምህርት ቤቶች ላይ በመዘዋወር ስርቻለው. እንድሁም በኃላፊነት ከትምህርት ቤት ዳርክተርነት እስከ ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ (የወረዳው ከፍተኛ አመራር ) በመሆን እያገለገልኩኝ የመጀመርያ ድግሪ ትምህርቴንም 2006 ከጅማ ዩንቨርስቲ በgeography ተመረኩኝ. በመጨረሻም 2010 የአመራር የትምህርት ዕድል ስመጣ እንደወረዳ አንድ አመራር በሚፈለግበት አንደኛ በመሆን የሁለተኛ ድግሪ ትምህርት ጀመርኩኝ. የሁለተኛ ድግሪ ትምህርቴን በ ጅማ ኡኒቨርሲቲ በgeographic information system (GIS) የጥናት ፅሁፍ very good በማግኘት 2012 መጨረሻ ተመርኩ. ከ2012-14 የጅማ ዞን መሬት አስተዳደር የካዳስተር ስራህደት ባለሞያ በመሆን ካገለገልኩ ቡሃላ በ 2014 የልሙ ኮሳ ዎረዳን ሕዝብ በመዎከል የብልፅግና ፓርቲ የህዝብ ተዎካይ ምክር ቤት ተመራጭ በመሆን አዲስ አበባ ገባው. በዝህ 5 ዓመት ቆይታየም ለወከልኝ ሕዝብ እና ሀገር አቅሜ በፈቀደ መጠን የተለያዩ ሰራዎችን በመስራት, በመጠየቅ እናም በማወያየት የህዝቡ ጥያቄ እንድመለስ ጥረት በማድረግ ኃላፊነቴን በመወጣት ፓርቲው እና ህዝቡ የሰጠኝን አደራ በመወጣት ዳግም የ 7ኛ ዙር ተመራጭ ለመሆን ስለበቃዉ ልባዊ ደስታ እየተሰማኝ ለወደፊትም የተታለብኝን ትልቅ አደራ እና ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት እተጋለው. ባጠቃላይ የሕይወት ታሪኬ በአጭሩ ይህን ይመስላል.