ምክር ቤቱ በአንቀጽ 55፣ አንቀጽ 70(1)፣ አንቀጽ 79(4)(ሐ)፣ አንቀጽ 82(2)(ሐ)፣ አንቀጽ 101፣ አንቀጽ 102፣ አንቀጽ 103 እና... የተሰጡት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል።
የምርጫ ክልል
ጭልጋ 1
ክልል:
አማራ
በካርታው ላይ ለማየት ጠቅ ያድርጉ
የሕይወት ታሪክ
አጭር የሕይወት ታሪክ
አቶ አላምረው አበራ አያሌው የተወለዱት የካቲት 23 ቀን 1977 ዓ.ም. በጭልጋ ወረዳ፣ ጎንደር፣ አማራ ክልል ነው። የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸው ማጠናቀቅ ቀጥሎ የትምህርት ዝግጅታቸውን በተፈጥሮ ሀብት ልማትና ጥበቃ ዲፕሎማ በአላጌ የግብርና ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ በመከታተል ጀምረው፣ በመቀጠል በማኔጅመንት/ሥራ አመራር የመጀመሪያ ዲግሪ ከአልፋ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ አግኝተዋል። በቻይና ከሚገኝ ዩኒቨርስቲ ኦፍ ቢዝነስ ኤንድ ኢኮኖሚክስ በዓለም አቀፍ የቢዝነስ አመራር አስተዳደር (IEMBA) ሁለተኛ ዲግሪ አግኝተዋል።
የሥራ ልምዳቸውን በ1997 ዓ.ም. በጭልጋ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት የቀበሌ የተፈጥሮ ሀብት ልማትና ጥበቃ ባለሙያ በመሆን ጀምረዋል። ከዚያም በጭልጋ ወረዳ የሕዝብ ግንኙነት ምክትል ኃላፊ፣ የወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ እና የሕዝብ አደረጃጀት ጽ/ቤት ኃላፊ በመሆን አገልግለዋል።
በቀጣይም የላይ አርማጭሆ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ፣ የቀድሞ ሰሜን ጎንደር ዞን የገጠር ሕዝብ ግንኙነትና አደረጃጀት ምክትል ኃላፊ እና ኃላፊ ሆነው ሰርተዋል። ከ2012 ዓ.ም. ጀምሮ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ፣ የከተማና መሠረተ ልማት እና የሕዝብ አደረጃጀት ዘርፎችን በኃላፊነት መርተዋል። ከሚያዝያ 11 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ደግሞ የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምክትል ዋና አስተዳዳሪና የመሬት መምሪያ ኃላፊ በመሆን እየሠሩ ይገኛሉ።
አቶ አላምረው በረጅም የአመራር ዘመናቸው በገጠርና በግብርና ሙያ፣ በመንግሥት አስተዳደር፣ በከተማና ገጠር ልማት፣ በማህበራዊ ጉዳይና በሕዝብ አደረጃጀት ዘርፎች ሰፊ ልምድ አካብተዋል። በተጨማሪም በውጭ አገራት በተደረጉ የልምድ ልውውጥና የሥልጠና መርሃ ግብሮች በመሳተፍ የሙያና የአመራር አቅማቸውን አሳድገዋል።
በአመራር ባህሪያቸው ታታሪነት፣ የሥራ ተነሳሽነት፣ ማዳመጥና ከተለያዩ አካላት ጋር ተባብሮ የመሥራት ችሎታ የሚገለጽባቸው ሲሆን፣ በማህበራዊ ጉዳዮች በንቃት በመሳተፍና በማስተባበር የሚታወቁ ናቸው። በማንበብ፣ በልምድና በሥራ ላይ በመማር እውቀታቸውን በቀጣይነት ማዳበር የሚያምኑ ሲሆን፣ በተለያዩ የአመራርና የልማት ሥራዎች ውጤታማ ተሳትፎ አድርገዋል።