ምክር ቤቱ በአንቀጽ 55፣ አንቀጽ 70(1)፣ አንቀጽ 79(4)(ሐ)፣ አንቀጽ 82(2)(ሐ)፣ አንቀጽ 101፣ አንቀጽ 102፣ አንቀጽ 103 እና... የተሰጡት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል።
የምርጫ ክልል
ኦሮሚያ
ክልል:
ኦሮሚያ
በካርታው ላይ ለማየት ጠቅ ያድርጉ
የሕይወት ታሪክ
እኔ የተወለድኩት በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ጃርሶ ወረዳ ኤጀርሳ ጎሮ ቀበሌ በሐምሌ 12 1965 ነው፡፡ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቴን በጃርሶ 1ኛና መለስተኛ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከ1973-1978፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን በሐረር መድሃኔዓለም አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከ1979-1982 ተምሬያለሁ፡፡ ከዚያም በ1983 የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመግባት በ1986 የመጀመሪያ ዲግሪ በኢኮኖሚክስ ተመሪቄያለሁ፡፡ ከነሀሴ 5 1986 ጀምሮ በምዕራብ ሀረርጌ ፕላንና ኢኮኖሚ ልማት መመሪያ በአክስፐርትነት፣ ከ01/11/1987 ጀምሮ በመምሪያ ዳይሬክተርነት ለ 8 አመታት አገልግያለሁ፡፡ ከዚያም በኦሮሚያ ንግድ ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ በኢኮኖሚ አማካሪነት ከዚያ ደግሞ በምዕራብ ሐረርጌ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ኃላፊነት ሰርቻለሁ፡፡ ከነሀሴ 1995 ጀምሮ በቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ውስጥ የንግድና ኢንዱሰትሪ ልማት ኃላፊ በመሆኑ አስክ ሰኔ 30 1996 ሰርቻለሁ፡፡ ከዚያም በኦሮሚያ ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ በኤክስፐርትነት ከተመደብኩ በኋላ የማስተርስ ትምህርቴን ለመከታተል ሀረማያ ዩነቨርሲቲ ገባሁ፡፡ ከዚያም በ1999 በእርሻ ኢኮኖሚክስ ተመረቅሁ፡፡ ከዚያም የአዳማ ሪፈራል ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ በመmሆን ከ መስከረም 2000 ጀምሮ እስከ ህዳር 2004 ድረስ አገልጊያለሁ፡፡ ከዚያም አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በማዕከላዊ አስተዳደር ኃላፊነት ሰርቻለሁ፡፡ ከህዳር 2005 ጀምሮ የኢትዮጲያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ በመግባት ላለፉት 14 አመታት ከመምሪያ ዳይሬክተርነት እስከ ድርጅቱ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ ድረስ በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች አገልግያለሁ፡፡ ባለትዳና የሶስት ልጆች እንዲሁም የሶስት የልጅ ልጆች አሉኝ፡፡