ምክር ቤቱ በአንቀጽ 55፣ አንቀጽ 70(1)፣ አንቀጽ 79(4)(ሐ)፣ አንቀጽ 82(2)(ሐ)፣ አንቀጽ 101፣ አንቀጽ 102፣ አንቀጽ 103 እና... የተሰጡት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል።
የምርጫ ክልል
ዱርቤቴ
ክልል:
አማራ
በካርታው ላይ ለማየት ጠቅ ያድርጉ
የሕይወት ታሪክ
እኔ ማንጠግቦሽ ቸኮል አምባዬ በሰሜን ጎጃም ዞን በደ/አቸፈር ወረዳ በጉታ አድቢ ቀበሌ በ07/02/1981ዓ.ም ተወለድኩ፡፡እድሜ ለትምህርት ሲደርስ ከ1-7ኛ ክፍል በቢትወደድ አያሌው መኮንን 1ኛ ደረጃ ትም/ት ቤት ፣8ኛ ክፍል በዳንግላ መንገሻ ጀምበሬ 1ኛ ደረጃ ትም/ት ቤት እንዲሁም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን በዳንግላ ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት አጠናቅቂያለሁ፡፡ስለሆነም ለዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት በማምጣት የመጀመሪያ ዲግሪየን በአክሱም ዩኒቨርሲቲ በማርኬቲንግ ማኔጅመንት የትምህርት ዘርፈ ስከታተል ቆይቸ በ2003 ዓ.ም ትምህርቴን ካጠናቀቅሁ በኋላ ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ ወረዳወች በሹመት ስሰራ ቆይቸ ከ2013-2015 ዓ.ም የሁለተኛ ዲግሪ ትምህርቴን በአማራ ክልል ስቴት ዩኒቨርሲቲ በፕሮጀክት ማኔጅመት የትምህርት ዘርፍ ካጠናቀቅሁ በኋላ ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ በሜሪት እየሰራሁ እገኛለሁ፡፡