የሕይወት ታሪክ

እኔ አቶ መስፍን ኢልታሞ እቻ ከአባቴ ቀኛ አዘማች ኢልታሞ እቻ ቦሬ እና ከእናቴ እሜት ዘነበች ሳህሌ በሌ ታህሳስ 04 1960 ዓም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን ዲታ ወረዳ በአንዲሮ ግግሎ ቀበሌ ተወለጅያለሁ፡፡ ዕድምዬ ለትምህርት ሲደርስ ከ1-6ኛ ክፍል በአንድሮ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተከታተያለሁ፡፡ ሰባተኛ እና ስምንተኛ ክፍል ጨንቻ 1ኛና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተማርኩ ሲሆን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን በጨንቻ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተከታትዬ ጨርሻለሁ፡፡ በመቀጠል ሁለገብ ግብርና ትምህርት ዘርፍ ሰርትፍኬት፤በሰብል ልማት በደፕሎማ፤ በሶሾሎጂ እና ሶሻል አንትሮፖሎጂ ትምህትት መስክ በመጀምሪያ ድግሪ ተመሪቂያለሁ፡፡ በስራ መስክ በግብርና ባለሙያነት በቀበሌና በወረዳ ደረጃ ለ10ዓመት፤ ለ5 ዓመታት በተለያዩ ተቋማት በኃላፊነት መንግስትና ማህበረሰብን ያገለገልኩኝ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በግል ስራ መስክ ተሰማርቼ እገኛለሁ፡፡ እኔ አቶ መስፍን ኢልታሞ ባለትዳርና የ10 ልጆች አባት ነኝ፡፡ በሃገሪቱ ፖለቲካ ምህዳር ስፋት አንጻር በተፈጠረዉ ሚቹ ሁኔታ በ7ኛ ዉ ሐገራዊ ጠቅላላ ምርጫ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሳዊ ሪፖብልክ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን በዲታ ምርጫ ክልል የግል ዕጩ ተወዳዳሪ ሆኜ በመቅረብ በከፍተኛ (ከ95 ፐርሰንት በላይ) የመራጩ ህዝብ ድምጽ በማግኘት አሸንፌ አሁን የተወካዮች ምክር ቤት ስራ መጀመሪያ ጊዜን እየተጠባበኩ እገኛለሁ፡፡