ምክር ቤቱ በአንቀጽ 55፣ አንቀጽ 70(1)፣ አንቀጽ 79(4)(ሐ)፣ አንቀጽ 82(2)(ሐ)፣ አንቀጽ 101፣ አንቀጽ 102፣ አንቀጽ 103 እና... የተሰጡት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል።
የሕይወት ታሪክ
ዳምጠው ተሰማ ደነቀ በደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ በፖለቲካል ሳይንስ እና አለም አቀፍ ግንኑነት ትምህርት መስክ ረዳት ፕሮፌሰር ሲሆን ከማስተማር ስራዎች በተጨማሪ የተለየያዩ የንግድ፣ የፖለቲካ እና የሲቪክ ተቋማትን በመምራት ሙያዊ አበርክቶዎች እያደረገ የሚገኝ የ42 አመት ጎልማሳ ነው፡፡
ዳምጠው ተሰማ ከአባቱ አቶ ተሰማ ደነቀ በዜ ከእናቱ ከወ/ሮ ዳመነች ካሰኝ ህዳር 12 ቀን 1976 ዓም በመንዝ ቀያ ገብርኤል ወረዳ ተወለደ። ለአባቱ ለአቶ ተሰማ አስረኛ ልጅ ሲሆን ለእናቱ ደግም ከአምስቱ ልጆቿ አንዱና የመጀመሪያ ልጇ ነው። አስተዳደጉን በተመለከተ ገና በተጸነሰ በስድስት ወሩ እናትና አባቱ በመፋታታቸው አናቱ ወደቤተሰቦቿ በመመለሷ አያቶቹ ጋር ተወልዶ እስከ 12 አመቱ ድረስ ከሴት አያቱ ዘንድ ነው ያደገው። ከአያቶቹ ዘንድ ለስራ የደረሰ ወንድ ልጅ ባለመኖሩ ገና ከስድስት አመቱ ጀምሮ ከወንድ አያቱ አቶ ማናህሎ ገብረስላሴ ጋር ወደ እረኝነትና ወደግብርና ስራ ይሰማራ ነበር። አብሯቸው በግብርና ስራ ሲኳትን ውሎ ከስራ እንደተመለሱ ማታ ማታ መሰረታዊ የኃይማኖት፣ የፊደልና የንባብ ትምህርቶችን ያስተምሩት ነበር። ይህም እድሜው ከሰባት ከወራቶች ሲሆን ወደ መደበኛ ትምህርት ሲገባ ከእድሜ እኩዮቹ የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ አግዞታል።
በ1984 ዓ.ም. አንደኛ ክፍል በያኔዋ ቆላቆ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንደተቀላቀለ በመጀመሪያው መወሰነ ትምህርት ፈጣን የንባብና የጽሁፍ አቅም ካላትቸው አምስት ተማሪዎች የመጀመሪያውን ደረጃ ይዞ ወደሚቀጥለው ክፍል በመሸጋገር በአንድ አመት ሁለት ክፍሎችን ማለፍ ቻለ።በቀጣዩም አመት በተመሳሳይ መልኩ የላቀ ውጤት በማስመዝገብ በሁለት አመት ውስጥ ወደአምስተኛ ክፍል በመዘዋወር የመደበኛ ትምህርትን የቀጠለ ሲሆን ሌላውን የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ወልቂጤ ከተማ በሚገኙት ሰላም በር እና ራስ-ዘ ስላስሴ በሚባሉ ትምህርት ቤቶች ነው ያጠናቀቀው፡፡ አንደገናም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በደቡብ ክልል በየም ልዩ ወረዳ (በአሁኑ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ የም የዞን) ፎፋ ሁለተኛ ደረጃ ቤት ተከታትሎ ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ ወደቀድሞው ቅየው ወልቂጤ ከተማ ተመልሶ የመሰላዶ ትምህርቱን በጎሮ አጠቃላይ መሰናዶ ትምህርት ቤት ተከታትሎ በከፍተኛ ነጥብ አጠናቆ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ተቀላቅሏል፡፡ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቴ “በፖለቲካል ሳይንስና አለም አቀፍ ግንኙነት (ሜጀር) እና ማነጅመንት (ማይነር)” የመጀመሪያ ድግሪውን በ1998 ዓ.ም. አንዳገኘ በሀገር በመከላከያ ሚኒስቴር በመረጃ ዋና መመሪያ በግልጽ ምንጭ መረጃ ክፍል “በመቀጠናዊ መረጃ ስራዎችና በመረጃ ትንተና የስራ መደብ” ለሰባት አመታት አገልግሏል፡፡ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቶ እያገለገለ ሁለተኛ ድግሪውን በአለም አቀፍ ግንኙነት ትምህርት መስክ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተከታትሎ አጠናቋል፡፡ በመቀጠልም የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ለሁለት አመት ገደማ ካገለገለ በኋላ በነሃሴ 12 ቀን2007 ዓ.ም. የአለም አቀፍ ግንኙነት በሌክቸረርነት መደብ በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ በመቀጠር አምስት አመት ገደማ አገልግሏል፡፡ የአሳሳ ዩንቨርሲቲን ከመቀላቀሉ በፊት በመንግስት መስሪያ ቤቶች ከሚሰጠው መደበኛ አገልግሎት በተጨማሪ በምኒልክ ነርሲንግ ኮሌጅ እና በአዲስ አባባ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በስነ-ዜጋና ስነ-ምግባር ኮርስ ለተከታይ ሰባት አመታት በተጋባዥ መምህርነት (part-timer) አስተምሯል፡፡
በአሶሳ ዩኒቨርሲቲው ከማስተማር ስራው ጎን ለጎን የጥናትና ምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ፖሮጀክትን ከማከናወን በተጨማሪ የተለያዩ ምርምሮችን በኣዳሚያዊ ጆርናሎች አሳትሟል። በአካዳሚው ዘርፍም በ2011 ዓም ከአሶሳ ዩኒቨርሲቱ የረዳት ፕሮፌሰር እድገት ማግኘት ችሏል፡፡ በመጨረሻም በ2012 ዓ.ም. ጀምሮ በዝውውር ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲን በመቀላቀል በማስተማር፣ በችግር ፈቺ ምርምሮችና በማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮጅክቶች በማሳተፍ አገልግሎት እየሰጠ ያለ የአካዳሚክ ማህበረሰቡ አባል ነው፡፡
ከአከዳሚያዊ ስራዎች በተጨማሪ ከ2016 ዓ.ም. ጀምሮ ሄንግዳ ሪል እስቴት ኃ/የተ/የግ/ማህበርን በምክትል ቦርድ ሰብሳቢነት እና በምክትል ማኑጂንግ ዳይሬክትርነት እያገለገለ ትርፋማነቱን እያስቀጠላ የሚገኝ ሲሆን የሸዋ ሰላምና ልማት ማህበርንም (ሸዋሰማ) ከ2013 እስከ ከ2016 ዓ.ም. በቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅነት እና ከ2016 ዓም ጀምሮ በዋና ስራ አስኪያጅነት እየመራ በሀገራዊ ሰላም፣ በልማትና በተራድዖ ተግባራት አሻራውን እያሳረፈ ያለ እና ራሱን በተለያዩ የአመራርነት ዘርፎች እያበቃ የሚገኝ ሀገር ወዳድ ነው፡፡
በፖለቲካ ተሳትፎ አብንን አደራጅተው ለተቋማዊነትና ለስትራቶጃዊ የትግል መርህ ቅድሚያ በመስጠት ፓርቲውን አጠናክረው ካስቀጠሉ ከፍተኛ አመራሮች አንዱ ነው፡፡ በከግንቦት 10ቀን 2010 እስከ መጋቢት 2012ዓ.ም. የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የውጭ ጉዳዮች ኃላፊ እንዲሁም ከ2016 ጀምሮ የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ ሆኖ በስራ አስፈጻሚነት እያገለገለ የሚገኝ እና በ2018 ዓ.ም. በተከናወነው በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ በመሃል ሜዳ ምርጫ ክልል አብንን ወክሎ ለተወካዩች ምክር ቤት አባልነት በከፍተኛ ድምጽ ምክር ቤቱን የተቀላቀለ የ42 አመት ኢትዮጵያዊ ፖለቲከኛ ነው፡፡