ምክር ቤቱ በአንቀጽ 55፣ አንቀጽ 70(1)፣ አንቀጽ 79(4)(ሐ)፣ አንቀጽ 82(2)(ሐ)፣ አንቀጽ 101፣ አንቀጽ 102፣ አንቀጽ 103 እና... የተሰጡት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል።
የሕይወት ታሪክ
እኔ ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ ኮሬ ዱቤ በከፍተኛ ትምህርት፣ ምህንድስና፣ በኢንዱስትሪ አስተዳደር፣ በሕዝብ አስተዳደር እና በፓርላማ ስራ ከሃያ ዓመታት በላይ ልምድ ያለኝ ምሁር፣ ተመራማሪ፣ የመንግስት ሰራተኛ እና ባለሙያ ነኝ። ስራዬን የጀመርኩት በ1989 በአቢጃታ ሶዳ አሽ ኢንተርፕራይዝ እና በአዳሚ ቱሉ ፀረ-ተባይ ፎርሙላሽን ሼር ኩባንያ የምርት ሂደት ሱፐርቫዘር በመሆን ሰርቻለሁ። ከዚያ በኋላ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጌዴኦ ዞን የውሃ፣ ማዕድን እና የኢነርጂ ሃብት ልማት መምሪያ ኃላፊ፣ የገጠር መሠረተ ልማት መምሪያ ኃላፊ እና የጌዴኦ ዞን ልማት ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ የመሳሰሉ በርካታ የመሪነት ሚናዎችን ተጫውቻለሁ።
ከ2000 እስከ 2005 በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ መምህርነት እና በኋላም የምህንድስና ኮሌጅ ዲን ሆኜ ከሰራሁ በኋላ የዶክትሬት ድግሪዬን አግኝቻለሁ። ከዚያም ከ2005 እስከ 2008 የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት በመሆን ያገለገልኩ ሲሆን፣ ረዳት ፕሮፌሰር በመሆነ በማስተማርና ምርመር ስራ አገልግያለሁ።
መስከረም 2014 ዓም ጀምሮ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (HoPR) ውስጥ አገልግያለሁ። የዕቅድ፣ የበጀት እና የፋይናንስ ቋሚ ኮሚቴ በመቀጠልም የመንግስት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ስብሳቢ ሆኜ እያገለገልኩ እገኛለሁ።