ምክር ቤቱ በአንቀጽ 55፣ አንቀጽ 70(1)፣ አንቀጽ 79(4)(ሐ)፣ አንቀጽ 82(2)(ሐ)፣ አንቀጽ 101፣ አንቀጽ 102፣ አንቀጽ 103 እና... የተሰጡት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል።
የሕይወት ታሪክ
የአመራር የሕይወት ታሪክ
የወ/ሮ መሠረት መስቀሌ አያኖ
ዋና ዳይሬክተር፣ የፌዴራል የመንግሥት ግዥና ንብረት ባለሥልጣን
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ
ወ/ሮ መሠረት መስቀሌ አያኖ ከሁለት አስርተ ዓመታት በላይ በሕዝብ አስተዳደር፣ በተቋማዊ አመራር፣ በፖሊሲ ትግበራ፣ በተቋማዊ ልማት፣ በገቢ አስተዳደር፣ በከተማ ልማት እና በመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ዘርፎች ሰፊና ተለዋዋጭ የሙያ ልምድ ያካበቱ ከፍተኛ የመንግሥት አመራር ናቸው።
ከሐምሌ 16 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ የፌዴራል የመንግሥት ግዥና ንብረት ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው እየመሩ ይገኛሉ። በዚህ ኃላፊነታቸውም የሀገሪቱን የመንግሥት ግዥና የንብረት አስተዳደር ሥርዓት በማሳደግ፣ በማዘመንና በማስተባበር ረገድ ስትራቴጂካዊ አመራር ይሰጣሉ። በተለይም ቅልጥፍና፣ ግልጽነት፣ ተጠያቂነት፣ ሙያዊነት፣ ዲጂታል ለውጥ እና የተሻለ የሕዝብ አገልግሎት ላይ አፅንዖት ይሰጣሉ።
የሙያ የአመራር ልምድ
ወ/ሮ መሠረት መስቀሌ የሙያ ጉዟቸውን በ1993 ዓ.ም. በካፋ ዞን፣ ጨታ ወረዳ በካያ ት/ቤት በመምህርነት ጀመሩ። ከ1993 በጀት አመት እስከ 1998 ዓ.ም. በትምህርት ዘርፍ በማገልገል የተማሪዎችን ዕውቀትና ክህሎት በማሳደግ የመጀመሪያ የሙያ ልምዳቸውን አካበቱ። የመምህርነት ልምዳቸውም በግንኙነት፣ በማስተማር፣ በአመራርና በማህበረሰብ ተሳትፎ ረገድ ጠንካራ መሠረት ፈጥሮላቸዋል።
ከዚያም በካፋ ዞን የሴቶች ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ እና የካፋ ዞን ምክር ቤት ጽ/ቤት ኃላፊ ሆነው አገልግለዋል። በተጨማሪም በመንግሥት ኮሙኒኬሽን፣ ባህልና ቱሪዝም ዘርፍ በሙያተኝነት እንዲሁም በቦንጋ ኤፍ ኤም ራዲዮ ተርጓሚና አርታኢ ሆነው ሰርተዋል።
ከሀምሌ 2004 እስከ ጥር 2005 ዓ.ም. በቦንጋ ከተማ አስተዳደር የሕዝብ ግንኙነት አማካሪ ሆነው አገልግለዋል። ከጥር 2005 እስከ ጥር 2008 ዓ.ም. ደግሞ የደቡብ ኢትዮጵያ ሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ሆነው ሰርተዋል።
ከ2008 ጥር እስከ 2011 ጥቅምት ዓ.ም. የደቡብ ኢትዮጵያ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ በመሆን በወጣቶች ልማትና በስፖርት ዘርፍ የሚከናወኑ ፕሮግራሞችን መርተዋል፣ አስተባብረዋል።
በ2011 ዓ.ም. ወደ ፌዴራል መንግሥት አመራር በመሸጋገር በፕላንና ልማት ኮሚሽን በሚኒስትር ዴኤታ ደረጃ ምክትል ኮሚሽነር ሆነው አገልግለዋል። ይህም በብሔራዊ ዕቅድ፣ በፖሊሲ ማስተባበር፣ በተቋማዊ አመራርና በልማት አስተዳደር ያላቸውን ልምድ አስፋፍቷል።
ከመጋቢት 2012 እስከ ሚያዝያ 2013 ዓ.ም. በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ሰርተዋል። በዚህ ኃላፊነት በከተማ ልማት፣ በግንባታ፣ በፖሊሲ ትግበራና በተቋማዊ ማስተባበር ረገድ ከፍተኛ የአመራር ሚና ተወጥተዋል።
ከሚያዝያ 2012 እስከ ሐምሌ 2016 ዓ.ም. በገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው አገልግለዋል። በዚህ ወቅት በገቢ አስተዳደር፣ በተቋማዊ አፈጻጸም፣ በሕዝብ አገልግሎትና በመንግሥት ፖሊሲዎች ትግበራ ላይ ከፍተኛ የአመራር ኃላፊነት ተወጥተዋል።
ከሐምሌ 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ የፌዴራል የመንግሥት ግዥና ንብረት ባለሥልጣንን በዋና ዳይሬክተርነት እየመሩ ይገኛሉ።
የተቋማዊ አመራርና የቦርድ ልምድ
ከመደበኛ የመንግሥት ኃላፊነታቸው በተጨማሪ ወ/ሮ መሠረት መስቀሌ በተለያዩ የፖለቲካ፣ የቦርድ፣ የሙያ ማህበራትና ማህበራዊ ተቋማት አመራር ላይ ሰፊ ልምድ አካብተዋል።
ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ እስከአሁን የብልጽግና ፓርቲ ምክር ቤት አባል በመሆን በማገልገል ላይ ይገኛሉ፡፡ ከ2011 ጀምሮ እስከ 2015 በፌደራል የብልጽግና ፓርቲ የሴቶች ሊግ ፕሬዝዳንት በመሆን አገልግለዋል።
ከ1997 አስከ 2002 ዓ.ም የደቡብ ብ/ብ/ህ/ክልል ምክር ቤት አባል በመሆን እንዲሁም ከ2013 እስከ 2018 የአዲስ አበባ ምክር ቤት አባል በመሆን አገልግለዋል፡፡
በኢትዮ ኢንጂነርንግ ግሩፕ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ እና በመድሀኒት ቅራቢ አገልግሎት ቦርድ አባል በመሆን እያገለገሉ ሲሆን ቀደም ሲል በዲሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የቦርድ አባል፣ በጅንካ ዩኒቨርሲቲ የቦርድ ሰብሳቢ፣ በአምቦ ዩንቨርስቲ ቦርድ ሰብሳቢ እና በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የቦርድ አባል ሆነው አገልግለዋል። እንዲሁም በኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም እና በEITI ኢትዮጵያ የቦርድ አባል ሆነው ሰርተዋል።
እንዲሁም ከ2002 እስከ 2009 ዓ.ም. የደቡብ ኢትዮጵያ ሴቶች ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ሲያገለግሉ፣ ከ1994 እስከ 1998 ዓ.ም. ደግሞ በካፋ ዞን ጨታ ወረዳ መምህራን ማህበር ሰብሳቢ ሆነው ሰርተዋል።
እነዚህ የአመራር ኃላፊነቶች በተቋማዊ አስተዳደር፣ በስትራቴጂካዊ ክትትል፣ በተጠያቂነት፣ በባለድርሻ አካላት ትብብር፣ በዕቅድ እና በውሳኔ አሰጣጥ ረገድ ሰፊ ልምድ እንዲያካብቱ አስችሏቸዋል።
ትምህርትና ሙያዊ ልማት
ወ/ሮ መሰረት በከተማ ልማት አስተዳደር (Urban Management) የማስተርስ ዲግሪ እና በቋንቋ ትምህርት (Language Education) የባችለር ዲግሪ አግኝተዋል።
በተጨማሪም በከፍተኛ አመራር፣ በፌዴራሊዝም፣ በአመራር ልማት፣ በመግባባት፣ በውሳኔ አሰጣጥ፣ በጥሩ አስተዳደር፣ በከተማ ልማት፣ በተቋማዊ አስተዳደርና በቴክኖሎጂ ዘርፎች በርካታ የሙያ ሥልጠናዎችን ወስደዋል።
በኬኒያ በፕሮጀክት አስተዳደርና ክትትል፤ በቻይና ኤይቦ የስልጠና ማዕከል የልማት አመራርና የቻይና የዕድገት ጉዞ ተሞክሮ ላይ፤ በኮሪያ የSaemaul Undong እና የግብርና ልማት ሥልጠና ተካፍለዋል። እነዚህ ዓለም አቀፍ የልምድ ልውውጥና የሥልጠና ተሞክሮዎች በልማት፣ በተቋማዊ ለውጥ፣ በማህበረሰብ ተሳትፎና በዘላቂ ልማት ላይ ያላቸውን እይታ አስፋፍተዋል።
የአመራር ብቃትና ክህሎት
ወ/ሮ መሰረት በስትራቴጂካዊ አመራር፣ በተቋማዊ አስተዳደር፣ በትንተናዊ አስተሳሰብ፣ በችግር ፈቺነትና በጠንካራ የግንኙነት ክህሎት የተጠናከረ ብቃት አላቸው።
ዋና የሙያ ብቃታቸው የሚያካትቱት፦
• ስትራቴጂካዊ አመራርና ተቋማዊ አስተዳደር፤
• የሕዝብ አስተዳደርና የፖሊሲ ትግበራ፤
• ስትራቴጂካዊና ተቋማዊ ዕቅድ ዝግጅት፤
• የተቋም ለውጥና የአፈጻጸም አስተዳደር፤
• የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር፤
• የገቢ አስተዳደር፤
• የባለድርሻ አካላት ትብብርና ግንኙነት፤
• ትንተናዊ አስተሳሰብና በማስረጃ ላይ የተመሠረተ ውሳኔ አሰጣጥ፤
• ችግር ፈቺነትና ግጭት አፈታት፤
• የሕዝብ ግንኙነትና የሕዝብ ንግግር፤
• የቡድን አመራርና ማስተባበር፤
• የአቅም ግንባታና የዕውቀት አስተዳደር፤ እና
• በርካታና ውስብስብ የተቋም ኃላፊነቶችን በብቃት ማስተዳደር ናቸው።
በመረጃና በቴክኖሎጂ ዘርፍም Microsoft Word፣ Excel፣ Access፣ PowerPoint፣ Internet Applications፣ Database Management፣ SPSS፣ EPI Info እና AI የመሳሰሉ መሳሪያዎችን የመጠቀም ብቃት አላቸው።
የምርምርና የዕውቀት ልምድ
ወ/ሮ መሰረት በሰሩባቸው ተቋማት ሁሉ ጥናትና ምርምር ስራዎችን በማቀድና በመምራት ያሰሩ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በተለያዩ የትምህርትና የማህበራዊ ልማት ጉዳዮች ላይ በምርምርና በጥናት ተሳትፈዋል። ከጥናት ልምዳቸው መካከል ሴቶች በሕዝብ ተቋማት በውሳኔ ሰጪና በአመራር ቦታዎች ያላቸው ተሳትፎ፣ የተማሪዎች የዘግይቶ መምጣት ችግር፣ የሴትና የተጎጂ/የተገለሉ ማህበረሰቦች ተማሪዎች የትምህርት ተሳትፎ ዝቅተኛነት እና የትምህርት ሽፋን ዝቅተኛነት ምክንያቶች ላይ ያካሄዷቸው ጥናቶች ይገኙበታል። እነዚህ የምርምር ልምዶች ውስብስብ ጉዳዮችን የመተንተን፣ ዋና ዋና ችግሮችን የመለየት፣ ማስረጃን የመገምገምና ተግባራዊ መፍትሔዎችን የማቅረብ ችሎታቸውን አጠናክረዋል።
የአመራር ፍልስፍናና የሙያ እሴቶች
የወ/ሮ መሰረት የአመራር ፍልስፍና በሕዝብ አገልግሎት፣ ተጠያቂነት፣ ተቋማዊ ብቃት፣ የቡድን ሥራ፣ ቀጣይነት ያለው ትምህርት እና ውጤት ተኮር አመራር ላይ የተመሠረተ ነው።
የሙያ ጉዟቸው ከመምህርነት ወደ አካባቢ አስተዳደር፣ የሴቶችና ወጣቶች ልማት፣ ዕቅድና ልማት፣ ከተማ ልማት፣ ገቢ አስተዳደር እና የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ድረስ የተዘረጋ ሲሆን፣ ይህም የተለያዩ የመንግሥት ተቋማትና የልማት ዘርፎች ተያያዥነትን በሰፊ እይታ እንዲረዱ አስችሏቸዋል።
በአመራር ሥራቸው ውጤታማ ግንኙነትን፣ ትብብርን፣ ተቋማዊ ተጠያቂነትን፣ ሙያዊ ታማኝነትንና ብቃት ያላቸው ቡድኖችን መገንባትን አጽንዖት ይሰጣሉ። በተጨማሪም የንባብና የታሪክ ጥናት ፍላጎት ያላቸው ሲሆን፣ ይህም ለቀጣይ ትምህርትና ለሰፊ የማህበራዊና ተቋማዊ ግንዛቤ ያላቸውን ቁርጠኝነት ያሳያል።
የአሁኑ ኃላፊነትና አስተዋጽኦ
ወ/ሮ መሰረት በአሁኑ ወቅት የፌዴራል የመንግሥት ግዥና ንብረት ባለሥልጣንን በዋና ዳይሬክተርነት በመምራት የኢትዮጵያን የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ሥርዓት ለማዘመንና ለማጠናከር እየሠሩ ይገኛሉ። እንዲሁም የብልጽግና ፓርቲ ምክር ቤት አባል በመሆን እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡ በአመራራቸው በተለይ ቅልጥፍናን፣ ግልጽነትን፣ ተጠያቂነትን፣ ሙያዊነትን፣ ዲጂታል ለውጥን፣ ተቋማዊ አቅምን እና የሕዝብ ሀብትን በአግባቡ መጠቀምን ማሳደግ ላይ ትኩረት ይሰጣሉ። በስትራቴጂካዊ አመራርና በተቋማዊ ማስተባበር በመታገዝ ዘመናዊ፣ ተጠያቂ፣ ግልጽ፣ ቀልጣፋና ለሕዝብ ፍላጎት ምላሽ የሚሰጥ የመንግሥት ግዥ ሥርዓት ለመገንባት እያበረከቱ ይገኛሉ።