ምክር ቤቱ በአንቀጽ 55፣ አንቀጽ 70(1)፣ አንቀጽ 79(4)(ሐ)፣ አንቀጽ 82(2)(ሐ)፣ አንቀጽ 101፣ አንቀጽ 102፣ አንቀጽ 103 እና... የተሰጡት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል።
የምርጫ ክልል
ኦሮምያ
ክልል:
ኦሮሚያ
በካርታው ላይ ለማየት ጠቅ ያድርጉ
የሕይወት ታሪክ
ስም ዝናቡ አብደኑር አባቦራ እባላለሁ ። በ1970 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል፣ በጅማ ዞን፣ በሰጠማ ወረዳ፣ ጋትራ 01 ቀበሌ ተወለድኩ። አባቴ አቶ አብደኑር አባቦራ ሲሆኑ እናቴ ወይዘሮ ሉባባ አወል ናቸው። ከወላጆቼ ታታሪነትን፣ ትህትናን፣ ቅንነትን ለሰው መኖርን ተምሬ አድጌያለሁ።
የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቴን በጋትራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተከታትዬ አጠናቅቄያለሁ። 9ኛ ክፍልን በአጋሮ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተምሬያለሁ። ከ10ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ድረስ ደግሞ በጅማ መሰናዶ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተምሬ ትምህርቴን አጠናቅቄያለሁ።
ከዚያ በኋላ በጅማ መምህራን ኮሌጅ በቋንቋ ትምህርት ዘርፍ ዲፕሎማ አግኝቻለሁ። ትምህርቴን በመቀጠል በአልፋ ዩኒቨርሲቲ በማኔጅመንት ትምህርት ዘርፍ የመጀመሪያ ዲግሪዬን አግኝቻለሁ።
የሥራ ህይወቴን በሐምሌ 1 ቀን 1996 ዓ.ም በመምህርነት ጀመርኩ። በዲፎ ማኒ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለአንድ ዓመት በመምህርነት አገልግያለሁ። በ1998 ዓ.ም በዚያው ትምህርት ቤት ዳይሬክተር በመሆን የአመራር ኃላፊነት ተረክቤ ሠርቻለሁ።
ከዚያም በሰጠማ ወረዳ የወጣቶችና ስፖርት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሆኜ አገልግያለሁ። በመቀጠል የሰጠማ ወረዳ አስተዳደር አማካሪ በመሆን በተለያዩ የመንግስት አስተዳደራዊ ጉዳዮች ላይ ሠርቻለሁ።
ከዚህ በኋላ የሰጠማ ወረዳ የሕዝብ አደረጃጀት፣ የሠራተኛና ማህበራዊ ዋስትና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ በመሆን አገልግያለሁ። በኋላም የሰጠማ ወረዳ አስተዳዳሪ ሆኜ በልማት፣ በመልካም አስተዳደር እና በሕዝብ አገልግሎት ዘርፎች ላይ በንቃት ሠርቻለሁ።
በመቀጠልም በሰጠማ ወረዳ የግብር አከፋፈል ቅሬታ ሰሚ የሥራ ሂደት መሪ በመሆን በፍትሃዊነትና በተጠያቂነት መርሆዎች መሠረት ሠርቻለሁ።
ከዚያ ወደ ጅማ ዞን በመዘዋወር በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ጽሕፈት ቤት ውስጥ በማህበራት ሽግግር፣ ሞዴል ማውጣት፣ ምርጥ ተሞክሮ ቅመራ እና ማሰፋፊያ ባለሙያነት ዘርፍ ባለሙያ ሆኜ አገልግያለሁ። በመቀጠል የጅማ ዞን የአደጋ ስጋትና ዝግጁነት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ በመሆን በአደጋ መከላከልና በዝግጁነት ሥራዎች ላይ ሠርቻለሁ።
በአሁኑ ወቅት በጅማ ዞን ሥራ ዕድል ፈጠራና ክህሎት ጽሕፈት ቤት ውስጥ በገበያ ልማት፣ ባዛርና ኤግዚቢሽን የሥራ ሂደት መሪ በመሆን እስከ ዛሬ ድረስ እያገለገልኩ እገኛለሁ።
በትምህርት፣ በመንግስት አስተዳደር፣ በሰው ኃይል ልማት፣ በማህበረሰብ አደረጃጀት፣ በወጣቶች ልማት፣ በሥራ ዕድል ፈጠራ እና በአደጋ ስጋት ቅነሳ ዘርፎች ከ20 ዓመታት በላይ የሥራ ልምድ አለኝ። በሥራዬ ሁሉ ታማኝነትን፣ ተጠያቂነትን፣ ፍትሃዊነትንና ለሕዝብ አገልግሎት ያለኝን ቁርጠኝነት መርሄ አድርጌ እሠራለሁ።
እኔ ባለትዳር እና የ 4 ልጆች አባት ነኝ.