የሕይወት ታሪክ

ስሜ አራርሶ ቢቂላ ኤሌሞ ስሆን ተወልጄ ያደኩት በቀድሞ ሀረርጌ ጠቅላይ ግዛት ሆቦራ አዉራጃ ደደር ከተማ መጋቢት 05/1954 ዓ.ም ነበር፡፡ ዕድሜዬ ለትምህርት ሲደርስ እዚያዉ የትዉልድ ከተማዬ ጊራዘማች አበራ ጊዛወ ት/ት ቤት ከዚያ ደግሞ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን ደደር ሁሌኛ ደራጃ ት/ት ቤት በመግባት እስከ 12ኛ ክፍል ተማርኩ፡፡ በማስቀጠል በጊዜዉ የነበረዉን የጭቆና ሥርዓት በኅይል ለመገርሰስ የኦሮሞ ነፃነት ግንባርን በመቀላቀል የኢሕአደግ መንግስት በትግል እሰኪገረሰስ ድረስ የትጥቅ ትግል እያደረኩ ነበር፡፡ ነገር ግን በሀገሪቱ በተፈጠረዉ የፖለቲካ ሽግግር ምክንያት ለድርጅቴ በተደረገዉ ሰላማዊ የትግል ጥሪ ምክንያት ወደ ሀገሬ ተመልሼ ሀገሬን እያገለገልኩ ሲሆን በአሁን ጊዜ የኦሮሚያ ሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ ሆኜ በማገልገል ላይ እገኛለሁ፡፡