የሕይወት ታሪክ

እኔ ወይዘሮ ፋሲካ ሻንቆ አሰናቀው የተባልኩት በምዕ/ ጎንደር ዞን በገንደውሃ ከተማ ቀበሌ 01 ከአባቴ ከአቶ ሻንቆ አሰናቀው ሞላልኝ ከእናቴ ከወ/ሮ ወርቅነሺ የሁሌ ታየ በቀን 03/10/1979 ዓ.ም ተወለድኩ፡፡ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን በገንደውሃ ከተማ አንደኛ ትምህርቴንና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን በአይከል ተማ አጠኛቅቂያለሁ፡፡ ዲፕሎማየን ደሴ መምህራን ኮሌጂ ያጠናቀኩሁ ሲሆን የመጀመሪያ ድግሬየን ጎንደር ዩኒቭርሲቲ አጠናቅቂያለሁ፡፡ ማስተርስ ዲግሬየን በጎንደር ዪኒቨርሰቲ በ1 የትምህርት ዘርፎች ተመርቂያለሁ፡፡ ይህም የመጀመሪያ ዲግሪየን በጅግራፊ የሁለተኛ ዲግሪየን ናቹራል ሪሶርሰ ኢንድ ኢንቨሮመንታል ማንጀመንት ትምህርት ናቸው፡፡ በተለያዩ የመንግስት ተቋማት በሃላፊነትና በባለሙያነት በቅንነት፣በታታሪነት እና በብቃት አገልግያለሁ ለዚህም ማረጋገጫ የሚሆኑ የተለያዩ የምስክር ወረቀቶች እና የስራ ልምዶች አሉኝ፡፡ የምኖርበትን ማህበረሰብን በበጎ ፈቃድ አገልግሎት በተለያየ መስክ አገልግያለሁ፡፡ በ2018 በተካሄደው አገር አቀፍ ምርጫ ብርፅግና ፓርቲን ወክዬ መተማ ወረዳ የምርጫ ክልል ተወዳድሬ በማሸነፍ የኢፊድሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ሆኛለሁ፡፡