የሕይወት ታሪክ

ከ አባቴ ከ አቶ ታደገ ንብረት እና ከ እናቴ ከወይዘሮ ደጅይጥኑ ባይለይ በ1980 ዓ.ም በ አማራ ክልል በምስራቅ ጎጃም ዞን ድጎ ፅዮን ከተማ ተወለድኩ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቴን በድግጣሞ አንደኛ ትምህርት ቤት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን በሞጣ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አጠናቅቄ ከዛም የመጀመሪያ ድግሪየን ከደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ እንዲሁም የሁለተኛ ድግሪየን በ ባህር ዳር ዩንቨርስቲ በእንግሊዘኛ ቋንቋ በመምህርነት ሙያ ተመርቂያለው:: ከዚያም በቢቡኝ ወረዳ በመምህርነትና በአመራርነት አገልግያለሁ:: ከዚያም በ 6ኛው ዙር ምርጫ ብልፅግና ፓርቲን በመወከል በድጎ ፂዮን ምርጫ ክልል ተወዳድሬ በማሸነፍ ስሰራ ቆይቻለሁ አሁንም በዚሁ ምርጫ ክልል ብልፅግና ፓርቲን በመወከል ተወዳድሬ አሸናፊ ሁኛለው::