ምክር ቤቱ በአንቀጽ 55፣ አንቀጽ 70(1)፣ አንቀጽ 79(4)(ሐ)፣ አንቀጽ 82(2)(ሐ)፣ አንቀጽ 101፣ አንቀጽ 102፣ አንቀጽ 103 እና... የተሰጡት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል።
የምርጫ ክልል
አማራ
ክልል:
አማራ
በካርታው ላይ ለማየት ጠቅ ያድርጉ
የሕይወት ታሪክ
ዶ/ር ማህተመ ኃይሌ- የህይወት ታሪክ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የጤና ዘርፍ በተለያዩ ኃላፊነቶች ፣ በወረዳ፣ በዞን፣ በተቋም እና በክልል ደረጃ የተለያዩ የአመራር እና የአስተዳደር ኃላፊነቶችን አገልግያለሁ ። ሙያዊ የስራ ልምዶቼም የሚከተሉትን ያካትታል፡፡
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና የደሴ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዲን በመሆን አገልግያለሁ።
በዞን ደረጃ፣ በደቡብ ወሎ ዞን ጤና መምሪያ ውስጥ በበርካታ የአመራር ሚናዎችን ሰርቻለሁ፤ ከእነዚህም ውስጥ የዞኑ ጤና መምሪያ የጤና አገልግሎት እና የሥልጠና ዘርፍ ኃላፊ ፡ የስነ-ምግብ ፣ የኤችአይቪ/ኤድስ፣ የክትባት እና የህዝብ ጤና ድንገተኛ አደጋ አስተዳደር ቡድን መሪ በመሆን አገልግያለሁ ።
በወረዳ ደረጃ፣ በኮምቦልቻ እና ኩታበር ዲስትሪክት የጤና ጽ/ቤቶች ኃላፊ ሆኜ አገልግያለሁ፣ በእነዚህም ኃላፊነት በጤና አገልግሎት አሰጣጥ፣ በፕሮግራም አተገባበር፣ በሕዝብ ጤና አስተዳደር እና በጤና ስርዓት አስተዳደር አገልግያለሁ፡፡
ከአመራር ኃላፊነቶቼ ጎን ለጎን፣ ሳይንሳዊ ጽሑፎችን በማሳተም ለጤና ጥናትና ማስረጃ በማመንጨት ረገድ አስተዋጽኦ አድርጌያለሁ።
በተጨማሪም የኢትዮጵያ የቤተሰብ አመራር ማህበር (FGAE)፣ የወሎ ዩኒቨርሲቲ፣ የደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር ቀይ መስቀል ቅርንጫፍ እና የደሴ ጤና ጤና ጣቢያ የቦርድ አባል በመሆን በማገልገል ለተቋማዊ እና ለማህበረሰብ ልማት አስተዋጽኦ የማድረግ እደል አግኘቼ ሰርቻለሁ።