ምክር ቤቱ በአንቀጽ 55፣ አንቀጽ 70(1)፣ አንቀጽ 79(4)(ሐ)፣ አንቀጽ 82(2)(ሐ)፣ አንቀጽ 101፣ አንቀጽ 102፣ አንቀጽ 103 እና... የተሰጡት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል።
የምርጫ ክልል
ኦሮምያ
ክልል:
ኦሮሚያ
በካርታው ላይ ለማየት ጠቅ ያድርጉ
የሕይወት ታሪክ
እኔ በ1966 ዓ.ም. በኦሮሚያ ክልል፣ ምዕራብ ወለጋ ዞን፣ ቦጂ ወረዳ በሚገኝ ገጠር ቀበለ፣ ከገበሬ ቤተሰብ ተወለድኩ። ያደግሁበት የቤተሰብ አካባቢ በትጋት፣ በሥራ ፍቅር፣ በአብሮነትና በማኅበራዊ ኃላፊነት የሚያምን ነበር። ከልጅነቴ ጀምሮ ትምህርትን እወድ ስለነበር፣ በተለያዩ ችግሮች ውስጥም ቢሆን ትምህርቴን ለመቀጠል በመሥራቴ የሕይወቴ ጉዞ ጠንካራ መሠረት ሆኖኛል። የመጀመሪያና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን በተወለድኩበት አካባቢ ካጠናቀቅኩ በኋላ፣ በ1986 ዓ.ም. ከHawassa College of Agriculture ግብርናና የሰብል ምርት ዲፕሎማ፣ በ2000 ዓ.ም. ከHaramaya University በእፅዋት ሳይንስ የBSc፣ በ2004 ዓ.ም. ከJimma University በተፈጥሮ ሀብት አስተዳደር የMSc፣ እንዲሁም በ2017 ዓ.ም. ከAddis Ababa University በምግብ ዋስትናና ልማት የPhD ዲግሪ አግኝቻለሁ።
ከሁለት አስርተ ዓመታት በላይ ባካበትኩትየሙያ ልምድ ከበወረዳ ጀምሮ እስከ ዞን ክልልና አገር አቀፍ በተለያዩ ደረጃ በቴክኒክና በአመራር ኃላፊነቶች ሰርቻለሁ። ከመንግሥት አገልግሎቴ በተጨማሪ፣በየተባበሩት መንግሥታት የምግብና ግብርና ድርጅት (FAO) ኢትዮጵያ የሀገር አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ባለሙያ በመሆን አገልግያለሁ።በተጨማሪም ለተለያዩ ሀገር አቀፍና ዓለም አቀፍ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና የልማት አጋሮች የቴክኒክ ተጠሪ (Technical Focal Point) እና የቴክኒክ አማካሪ በመሆን ሰፊ የዓለም አቀፍ የሥራ ልምድ አግኝቻለሁ።
ከ2013 ዓ.ም. ጀምሮ 6ኛዙር የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል በመሆንእውቀቴን፣የሥራ ልምዴን እና የአመራር ተሞክሮዬን በማበርከት ላይ እገኛለሁ።በተጨማሪም በማህበረሰብ አቅም ግንባታ ያካበትኩትን ሰፊ ልምድ በመነሻ በማድረግ “ግሪን ዎክ ኢትዮጵያ (Green Walk Ethiopia) ያልሆነ ድርጅት መሥራች በመሆን ያካበትኩትን የሙያና የአመራር ልምድ በአካባቢ ጥበቃ፣ በዘላቂ ልማት፣ በማኅበረሰብ አቅም ግንባታና በአየር ንብረት ላይ ለማበርከት እየሠራሁ እገኛለሁ።
በቀጣይም ያካበትኩትን እውቀትና ልምድ ለሕዝብ ጥቅም በኃላፊነት በማዋል፣ አካታች፣ ሰላማዊ፣ ጽኑ፣ አካባቢን የሚጠብቅ እና ዘላቂ የሆነች ኢትዮጵያን ለመገንባት የራሴን አስተዋፅኦ ማድረግ የቀጣይ ጉዞዬ ዋና አቅጣጫ ይሆናል።