ምክር ቤቱ በአንቀጽ 55፣ አንቀጽ 70(1)፣ አንቀጽ 79(4)(ሐ)፣ አንቀጽ 82(2)(ሐ)፣ አንቀጽ 101፣ አንቀጽ 102፣ አንቀጽ 103 እና... የተሰጡት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል።
የምርጫ ክልል
Burji
ክልል:
ደቡብ
በካርታው ላይ ለማየት ጠቅ ያድርጉ
የሕይወት ታሪክ
ዶ/ር ዮሐንስ ማሬ ጎሎ እባላለሁ፡፡ በጥቂምት 22/1962 ዓ ም. ከአባቴ አቶ ማሬ ጎሎ እና ከእናቴ ወ/ሮ ሐጌ ሳጌ በወቅቱ አጠራሪ ሲዳሞ ክፍለ አገር በአሬሮ አዉራጃ በቡርጂ ወረዳ በረለያ ቀበሌ ተወለድኩኝ፡፡ ዕድሜዬ ለትምህርት ስደርስ የአንደኛ ደረጃ ትምህርቴን በአርብቾ፤ በሴጎ፤ በጋምቦ እና በሶያማ አንደኛ ደረጃ ት/ ቤቶች ተዘዋዉሬ ተማርኩኝ፡፡ በ1973 -1974 ዓ. ም. የ7ኛ እና 8ኛ ክፍል ትምህርቴን በቀድሞ አጠራሪ ሃገሬማሪያም በአሁኑ አጠራሪ በቡሌ ሆራ ከተማ ተማርኩኝ፡፡ ከ9ኛ እስለ 12ኛ ክፍል በያቤሎ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በማጠናቀቅ በ1979 ዓ. ም. - 1980 ዓ. ም. በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአዋሳ መለስተኛ እርሻ ኮሌጅ በዕጽዋት ሳይንስና ቴክኖሎጂ በድፕሎማ ተመረቅሁኝ፡፡ ከ1981 እስከ 1990ዓ. ም. ድረስ ከልማት ጣቢያ ሰራተኝነት ጀምሮ እስከ ልዩ ወረዳ አስተዳደርነት ድረስ በተለያዩ የሃላፊነት ደረጃዎች ህብረተሰቡን ካገለገልኩኝ በኋላ በ1991 ዓ. ም. ለመጀመሪያ ድግሪ ትምህርት ሃራማያ ዩኒቨርሲቲ ገባሁኝ፡፡ ከዚያም በ1993 ዓ. ም. በግብርና ኤክስቴንሽን የመጀመሪያ ድግሪ አገኘሁ፡፡ ወደ ቡርጂ ልዩ ወረዳ በመመለስም ለ6 ዓመት ከሠራሁኝ በኋላ በ2000ዓ. ም. ለሁለተኛ ድግሪ ሃራማያ ዩኒቨርሲቲ እንደገና ተመልሼ በ2001 ዓ. ም. በገጠር ልማትና በግብርና ኤክስቴንሽን ተመረቅሁኝ፡፡
2ኛ ድግሪዬን ከተቀበልኩኝ በኋላ በ2002 ዓ. ም. በጥቂምት ወር አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በግብርና ሳይንስ ኮሌጅ በመምህርነት ተቀጠርኩኝ፡፡ ከጥቂምት 20002 ዓ. ም. ጀምሮ እስከ 2008 ዓ. ም. በግብርና ሳይንስ ኮሌጅ የምርምር ዘርፍ አስተባባሪነት እና በገጠር ልማትና ግብርና ኤክስተንሽን ት/ ክፍል ሃላፍነት ሳገለግል ቆይቼ ለ3ኛ ድግሪ በ2009 ዓ. ም. ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ገብቼ ትምህርቴን ጀመርኩኝ፡፡ ከዚያም በ2013 ዓ. ም. በኑሮ ዘዴና ድህነት ቅነሳ ( Livelihoods and Poverty Reduction) 3ኛ ድግሪዬን በከፍተኛ ማዕረግ አጠናቀቅሁኝ፡፡
ከ2014 ዓ. ም. ጀምሮ ከአስተማሪነት ጎን ለጎን የገጠር ልማትና ግብርና ሳይንስ ት/ክፍልን በሃላፍነት ከመራሁኝ በኋላ በ2015 ዓ. ም. በግብርና ሳይንስ ኮሌጅ ም/ዲን ሆኜ ሥራዬን የጀመርኩ ሲሆን እስከአሁኑ ሰዓት በዚያዉ ሃላፊነት እየሰራሁ እገኛለሁ፡፡ በዩቨርሲቲ ቆይታዬ በተለያዩ ክፍሎች በሃላፊነት ከማገልገሌ ጎን ለጎን የማስተማሪንና የምርምር ሥራዎችን በትጋት በመሥራት ከመጀመሪያ ድግሪ ተመራቀዎች በተጨማሪ ከ20 በላይ የሁለተኛ ድግሪ ተማሪዎችን በዋና አማካሪነት በመምራት በጥሩ ዉጤት ትምህርታቸዉን እንዲጨርሱ አድርጌአለሁ፡፡ በምርምር ሥራም በርካታ የምርምር ሥራዎችን በዋና ተመራማሪነት የሠራሁ ሲሆን ከዘጠኝ በላይ የምርምር ጽሁፎችን በዓለም ዓቀፍ ታዋቂ ጆርናሎች ላይ አሳትሜአለሁኝ፡፡
እኔ ባለ ትዳርና የ4 ወንድ እና የ2 ሴት ልጆችን ከባለቤቴ ወ/ሮ መስተዋት ዎቼ አፍርቼአለሁኝ፡፡ የፖለቲካ ተሳትፎዬን በተመለከተ በቡርጂ ህዝቦች ዲምክራሲያዊ አንድነት ም/ ሊቀመንበር ሆኜ የደኢህደን ሥራ አስፈጻም እና የኢህአዴግ ም/ቤት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል በመሆን አገለግያለሁ፡፡ ከዚያያም በ7ኛ አገራዊ ምርጫ የብልጽግና ፓሪትን በመወከል ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባልነት ተወዳድሬ አሸንፌለሁኝ፡፡ በሆኑም ከ2019 ዓ. ም. ጀምሮ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት በአባልነትና ፓሪትዬና መንግሥት በሚመድበኝ ቦታ ህብረተሰቤንና አገሬን ለማገልገል ተዘጋጅቻለሁ፡፡