የሕይወት ታሪክ

እኔ አንሻ ሰይድ እብራሂም በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር በቢራሮ ክ/ከተማ በ1968 ዓ/ም ከአባቴ በግብርና ስራ ከሚተዳደሩት አቶ ሰይድ እብራሂም እና ከእናቴ ወ/ሮ ማስረሻ አደም ተወለድኩ፡፡ እድሜየ ለአቅመ ትምህርት ሲደርስ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቴን በሰርደም አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ፤ከ7-8ኛ ክፍል በኮምቦልቻ ጁኔር ት/ቤት፤ የ2ኛ ደረጃ ትምህርቴን በኮምቦልቻ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ1986 ዓ/ም አጠናቀቅኩኝ ፡፡የ2ኛ ዲግሪ ትምህርቴን የከፍተኛ ማእረግ እና የሜዳሊያ ተሸላሚ በመሆን አጠናቅቄአለሁ፡፡