ምክር ቤቱ በአንቀጽ 55፣ አንቀጽ 70(1)፣ አንቀጽ 79(4)(ሐ)፣ አንቀጽ 82(2)(ሐ)፣ አንቀጽ 101፣ አንቀጽ 102፣ አንቀጽ 103 እና... የተሰጡት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል።
የሕይወት ታሪክ
ስሜ ዶ/ር ግርማ እሸቱ ይባላል። የተወለድኩት በ1986 ዓ.ም. በኦሮሚያ ክልል ጂማ ዞን፣ ኖኖ ቤንጃ ወረዳ ሲሆን፣ ከአባቴ እሸቱ ተሾመ ኢታኣ እና ከእናቴ የሺ መንግስቱ ጀመማ በኤብቻ የገጠር ቀበሌ ተወለደኩ፡፡ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቴን እዛው በሚገኘው የቆጦኦና አልጋ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት (1-8) የጀመርኩ ሲሆን፣ በመቀጠልም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን በጂማ ከተማ ሰጦ ሰመሮ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ተከታተልኩ። ከዚያም በጂማ ዩንቨርሲቲ በግብርና የመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪዬን፣ በቻይና ሀገር ሶስተኛ ዲግሪዬን ተከታትያለው፡፡ትምህርቴን እንደጨረስኩም በጅማ ዞን በኖኖ ቤንጃ ወረዳ የኅብረት ሥራ ማህበራት ማስፋፊያ ጽሕፈት ቤት ውስጥ ኃላፊ ሁኜ ስረቻለው፣ ከዚያም የሁለተኛ ዲግሪ (Postgraduate) ትምህርቴን አጠናቅቄ የፌደራል ምርምር ተቋም የሆነውን የኢትዮጵያ ብዝሃ ሕይወት ኢንስቲትዩትን ተቀላቀልኩ። በኢንስቲትዩቱ ውስጥ በተመራማሪነት፣ በሀረር ማዕከል ዳይሬክተርነት፣ በፕሮጀክት አስተባባሪነት እንዲሁም በሥራ አመራር አባልነት ከፍተኛ አገልግሎት አበርክቻለሁ። በተጨማሪም ጂማ ዞን ሊሙ ሰቃ ምርጫ ክልል በመወከል የጨፌ ኦሮሚያ አባል ሆኜ አገልግያለሁ።በሙያ ዘመኔ በኢትዮጵያ ብዝሃ ሕይወትና ግብርና ዙሪያ ከ20 በላይ ሳይንሳዊ ጽሑፎችንና መጻሕፍትን ያሳተምኩ ሲሆን፣ በበርካታ ዘርፎች ላይ የአሰልጣኝነትና የባለሙያ አማካሪነት (Consultancy) አገልግሎት ሰጥቻለሁ።