ምክር ቤቱ በአንቀጽ 55፣ አንቀጽ 70(1)፣ አንቀጽ 79(4)(ሐ)፣ አንቀጽ 82(2)(ሐ)፣ አንቀጽ 101፣ አንቀጽ 102፣ አንቀጽ 103 እና... የተሰጡት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል።
የምርጫ ክልል
ኦሮሚያ
ክልል:
ኦሮሚያ
በካርታው ላይ ለማየት ጠቅ ያድርጉ
የሕይወት ታሪክ
የዶ/ር አዱኛ ደበላ ቦቴ የሙያ ታሪክ መግለጫ
ዶ/ር አዱኛ ደበላ ቦቴ በግብርና ሳይንስ ዘርፍ ከ26 ዓመታት በላይ የተግባር ልምድ ያለው፣ በቡና፣ ሻይ እና ቅመማ ቅመሞች ኢኮ-ፊዚዮሎጂ፣ አግሮኖሚ እና የእሴት ሰንሰለት ልማት ላይ የተሟላ ዕውቀትና ልምድ ያካበተ ባለሙያና ራዕይ ያለው የሴክተር መሪ ነው። ከጠንካራ የተቋማዊ አመራር አቅም ጋር በማጣመር፣ በማስረጃ ላይ የተመሠረተ ፖሊሲ ቀረጻ፣ ስትራቴጂክ ዕቅድ እና ውጤታማ የባለድርሻ አካላት ትብብርን በመጠቀም የኢትዮጵያን የቡና ዘርፍ ከፍ እንዲል በመሪነት ሚና የተሳተፈ ነው።
በበርካታ ዘርፎች የተዋቀሩ ቡድኖችን በመምራት፣ የወጪ ንግድ ማበረታቻን በማስፋፋት፣ ኢንቨስትመንትን በማንቀሳቀስ እና በግብርና ምርትና ግብይት ዘርፍ ፈጠራን በማስፋፋት የተረጋገጠ የሥራ አፈጻጸም ሪከርድ እንዲመጣ የራሱን አስትዋጽኦ እየተወጣ ያለ የሴክተር መሪ ነው። ከአውሮፓ ህብረት (EU)፣ ከግሎባል ኢንቫይሮንመንት ፋሲሊቲ (GEF)፣ ከጣሊያን መንግሥት፣ ከFAO እና ከUSAID ጨምሮ በርካታ ዋና ዋና አጋር ተቋማት የሚደግፏቸውን በሚሊዮኖች ዶላር የሚገመቱ ፕሮጀክቶችን በተሳካ ሁኔታ ቀርጾና መርቶ ውጤታማ እንዲሆኑ አድርጓል።
በቡና ፕሮጀክቶች ልማትና ትግበራ ላይ ከUNIDO ጋር በቅርበት በመስራት ላይ ይገኛል። በቡና፣ ሻይ እና ቅመማ ቅመሞች የአገር አቀፍ የእሴት ሰንሰለት ልማትና የግብይት ተነሳሽነቶችን በመምራት፣ በኢትዮጵያ የቡና ወጪ ንግድ መጠንና ገቢ ላይ ታሪካዊ ለውጥ በማምጣት ከ600 ሚሊየን በአምስት እጥፍ እድገት እንዲመዘገብ በማድረግ ሶስት ቢሊዬን ዶላር ለሃገር ገቢ እንዲገኝ አድርጓል። ይህም እስከዛሬ ከተመዘገቡት ከፍተኛ ውጤቶች መካከል የሚጠቀስ ነው።
በ2022/23 እና በ2023/24 የሥራ ዘመናት በኢንዱስትሪ አመራር ዘርፍ በላቀ የሥራ አፈጻጸም ያስመዘገበውን ልዩ አስተዋፅኦ በማረጋገጥ የ“Extraordinary Meritorious Performance” ሽልማት አሸንፏል።