የሕይወት ታሪክ

እ.ኤ.አ. በ1975 በጉራጌ ዞን ጉመር ወረዳ አረቅጥ ከተማ አቅራቢያ በእርሻ ሥራ ከሚተዳደሩ ወላጆች ተወለድኩ። የመጀመሪያ እና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን እስከ 8ኛ ክፍል በአረቅጥ የመጀመሪያና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተከታትያለሁ። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን በአዲስ አበባ መድኃኔዓለም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የቀጠልኩ ሲሆን፣ በ1994 አጠናቅቄአለሁ። በ1995 የአዲስ አበባንግድ ሥራ ኮሌጅ ገብቼ በባንክ እና ፋይናንስ የትምህርቶ መስክ በዲፕሎማ ተመረቅኩ። ባለትዳርና የአራት ልጆች አባት ነኝ። በምኖርበት አካባቢም የማኅበረሰብ መሪ በመሆን ላለፉት ሦስት ዓመታት እያገለገልኩ እገኛለሁ። በተጨማሪም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማኅበርን በሥራ አስፈጻማነትና በዋና ፀሐፊነት ተመርጬ ለ 3 ዓመታት አገልግያለሁ። የሙያ ጉዞዬ የጀመረው በኮንስትራክሽን እና ቢዝነስ ባንክ ለአጭር ጊዜ (21 ቀናት) ቆይታ በማድረግ ሲሆን፣ በ1996 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ተቀላቅዬ ከጁኒየር ባንክ ክለርክ ጀምሮ እስከ ዋና የጥናትና ምርምር (R&D) ኦፊሰርነት በተለያዩ የኃላፊነት መደቦች እስከ 2016 ድረስ ሠርቻለሁ፤ ከዚያም ወደ አቢሲኒያ ባንክ ተዛወርኩ። ግንቦት 2016 በአቢሲኒያ ባንክ የንግድ ልማት ሥራ አስኪያጅ በመሆን ተቀላቅዬ፣ የምርምር እና ትንተና ሥራ አስኪያጅ፣ እንዲሁም የስትራቴጂ እና ቢዝነስ እቅድ ሥራ አስኪያጅ በመሆን እስከ ታኅሣሥ 2021 አገልግያለሁ። ከዚያም አማራ ባንክን በምርምርና ልማት ዳይሬክተርነት የተቀላቀልኩ ሲሆን፣ እስከ ሚያዝያ 2025 በዚያው ቆይቼ በመቀጠል ንብ ኢንተርናሽናል ባንክን በምርምርና ልማት ዳይሬክተር፣ የቢዝነስ ፕሮግራሞች ዳይሬክተር፣ እና በመጨረሻም እስከ ዛሬ ድረስ የኢንቨስትመንት ማኔጅመንት ዳይሬክተር በመሆን እያገለገልኩ እገኛለሁ። የፖለቲካ እንቅስቃሴዎችን በንቃት የምከታተልና በተለያዩ የውይይት መድረኮች ላይ የምሳተፍ ቢሆንም፣ የተደራጀ የፓርቲ ፖለቲካ ጉዞዬ የጀመረው የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ፓርቲ ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ ነው። በአባልነት ጀምሮ፣ ከ6ኛው ለገራዊጨምርጫ ማግስት የትይዩ ካቢኔ አባል፣ የትይዩ ካቢኔ ጸሐፊ፣ የብሔራዊ ሥራ አስፈጻሚ አባልን ጨምሮ ከፍተኛ የአመራር ኃላፊነቶችን በመያዝ የቆየሁ ሲሆን አሁን ደግሞ የፓርቲው ምክትል መሪ በመሆን እያገለገልኩ ይገኛለሁ።