የሕይወት ታሪክ

እንደግ አዳነ ይታየው እባላለው ። ከእናቴ ከወ/ሮ ዘውዴ ባንቴ እና ከአባቴ ከአቶ አዳነ ይታየው በ1983 ዓ.ም በምስ/ጎጃም ዞን በጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ በ04 ቀበሌ ተወለድኩኝ ። የትምህርት ሁኔታየ በ2006 ዓ.ም በዲፕሎማ በመምህርነት በ2017 ዓ.ም በመጀመሪያ ድግሪ በማንጅመንት የተመረኩኝ ሲሆን 2ኛ ድግሪየን በፖለቲካ ሳይንስ እያጠናው እገኛለው ። በመምህረነት 1 ዓመት አገልግያለው በደብረ ማርቆስ ከተማ ። የፖለቲካ ተሳትፎየ ከለውጡ በፊት በኤርትራ በርሃ በአርበኞች ግንቦት 7 በተለያየ ሓላፊነት በትጥቅ ትግል ህወሃት/ኢህአዲግን ታግያለው ። ከለውጡ በኋላ ወደ አገር ቤት በመግባት ኢዜማን ከመሰረቱ ሰዎች አንዱ ነኝ ። የኢዜማ የምስራቅ ጎጃም ዞን አስተባባሪ ሁኜ እየሰራው ነው ። የአማራ ክልል የፀጥታ ችግር ሲገጥመው ከሀገር መከላኪያ ሰራዊት ጎን በመቆም በመረጃ ስራ ሰርቻለው ፣ በምስ/ጎጃም ዞን በሰዴ ወረዳ የፀጥታ ክትትል የመረጃ ኦፊሰር እስከ አሁኗ ሰዓት ድረስ እየሰራው እገኛለው ። ከወንበዴ/ፅፈኛ ቡድን ጋር ፊት በመግጠም በቦንብ ከባድ የመቁሰል አዳጋ ጥር 21 በ2017 ዓ.ም የደረሰብኝ ሲሆን ፤ የትዳር ሁኔታየ የአገባሁና የ2 ልጆች ከባት ነኝ ።