የሕይወት ታሪክ

እኔ አቶ ጋሻው ዳኘው ላቀው እባላለሁ።በ1979 ዓ.ም በአማራ ክልል በደቡብ ጎንደር ዞን በስማዳ ወረዳ በአሰዴ አዳዳ ቀበሌ ተወለድኩ።የ1ኛ ደረጃ ትምህርቴን በሰዴ አዳዳ 1ኛ ደረጃ የተማርኩ ሲሆን የ2ኛ ደረጃ ትምህርቴን በስማዳ ወረዳ ታገል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማርኩ።የመጀመሪያ ድግሬን በመቀሌ ዩንቨርሲቲ በጆርናሊዝምና ኮሙኒኬሽን የተመረኩ ሲሆን 2ኛ ድግሪየን በሚዲያና ኮሙኒኬሽን ባህርዳር ዩንቨርስቲ የተማርኩ ሲሆን በተጨማሪም በቢዝነስ አስተዳደር 2ኛ ድግሪየን ከናሽናል ኮሌጅ ተመርቂያለሁ። ከ2000 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ ኃላፊነት ከወረዳ እስከ ዞን ባሉት ቦታዎች በሹመት እስከ 2013 ዓ.ም ያገለገልኩ ሲሆን ከ2014 ጀምሮ ለ6ኛው ዙር የምክርቤት አባላት በመመረጥ እስከ 2018 መጨረሻ ድረስ አገልግያለሁ።