የሕይወት ታሪክ

ሰሜ አቶ ተስፋው ግዛቸው ሲሆን የተወለድሁት በአማራ ክልል በምስራቅ ጎጃም ዞን በጎዛምን ወረዳ በየጥጃን ሸባልማ ቀበሌ ሲሆን ትሁትና ለጋስ ከሆኑት ቤተሰቦቸ ከአባቴ ከአቶ ግዛቸው አያሌው እንዲሁም ከእናቴ ከወይዘሮ ምንትዋብ አለሙ እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጥር ሰኔ 12 ቀን 1970 ዓ.ም ተወለድሁ ። አድሜየ ለትምርት እንደደረሰ የመጀመርያ ደረጃ ትምህርቴን በወንቃ አንደኛና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንዲሁም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን በደብረ-ማርቆስ አጠቃላይ ሁለተኛ ትምህርት ቤት፣ የመጀመርያ ድግሪና ሀለተኛ ድግሪየን በደብረ-ማርቆስ ዩኒቨርስቲ በህግ ትምህርት አጠናቅቂያለሁ ። አጠቃላይ የስራ ሁኔታ በመንግስት ስራ በየደረጃው በባለሙያነትበ እና በአመራርነት ለ23 ዓመት ለመንግስት በከፍተኛ ታማኝነትና ቅንነት አገልግያለሁ።