የሕይወት ታሪክ

የህይወት ታሪክ ከሊድስታር ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በአመራሪነት 2ኛ ዲግሪ (ማስተርስ) ያለኝ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅትም የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ) አባል ሆኜ እያገለገልኩ እገኛለሁ። ከወረዳ እስከ ፌዴራል ደረጃ በተለያዩ ኃላፊነቶች በመስራት ሰፊ የአመራር እና የሕዝብ አገልግሎት ልምድ አከብቻለሁ። በትምህርት ያገኘሁትን እውቀት ከተግባራዊ የአመራርና አገልግሎት ልምዴ ጋር በማዋሃድ የችግር አፈታትና የስራ ውሳኔ አሰጣጥ ክህሎቴን ከፍ አድርጌዋለሁ። ግቤ በትምህርት፣ በምርምርና በመልካም አስተዳደር ለሀገራዊ ልማት አዎንታዊ ተጽዕኖ መፍጠር ነው። በተለይም አካታች አመራርን በመተግበር፣ የቀጣዩ ትውልድ አርአያ በመሆን የጎላ ድርሻ እንዲኖራቸው ለማስቻል ነዉ።