የሕይወት ታሪክ

እኔ ግርማ ፈቃዱ ገለት እባላለሁ፤ ነሐሴ 30 ቀን 1974 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ጃርሶ ወረዳ (ሀሮ ብሩ ቀበሌ) ተወለድኩ። በትምህርት ዝግጅቴ ከሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በግብርና ኤክስቴንሽን የመጀመሪያ ዲግሪ (BSc)፣ እንዲሁም ከኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በከተማ ልማት ፕላኒንግ የሁለተኛ ዲግሪ (MA) በ 3.6 ከፍተኛ ማዕረግ ውጤት አግኝቻለሁ። ሙያዊ የሥራ ጉዞዬን በምዕራብ ወለጋ የጃርሶ ወረዳ ግብርናና ገጠር ልማት ጽ/ቤት ኃላፊነት የጀመርኩ ሲሆን፣ በመቀጠልም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጉለሌ ክፍለ ከተማ የወረዳ 08 ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የመሬት ዝግጅት ቡድን መሪ እና የመሬት ልማትና ከተማ ማደስ ጽ/ቤት ኃላፊ በመሆን፣ እንዲሁም በአራዳ ክፍለ ከተማ የመሬት ባንክና ማስተላለፍ ጽ/ቤት ኃላፊ በመሆን በተለያዩ ቁልፍ የአመራር እርከኖች ላይ በስኬት አገልግያለሁ። በአሁኑ ወቅትም ከሚያዝያ 2015 ዓ.ም ጀምሮ የአራዳ ክፍለ ከተማ ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ጽ/ቤት ኃላፊ በመሆን ተቋማዊ ዕቅዶችን፣ የመሬትና የከተማ ፕላን ልማትን እንዲሁም የሕዝብ አገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያ ሥራዎችን በበላይነት እየመራሁና እያስተባበርኩ እገኛለሁ።