የሕይወት ታሪክ

ወ/ሮ የዝና ደስታ ቦጋለ እባላለሁ የተወለድኩት በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በምዕራብ ጎጃም ዞን ልዩ መጠሪያው ጅጋ ከተማ ነው። የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቴን በትውልድ ቦታዬ ጅጋ ጥቁር ውሃ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት እንዲሁም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት በፍኖተ ሠላም ከተማ ዳሞት መሠናዶ ት/ቤት በመማር አጠናቅቄያለሁ። የከፍተኛ ደረጃ ትምህርትን በተመለከተ ቅድሚያ በደ/ብርሃን መምህራን ማሰልተኛ ተቋም በአንደኛ ደረጃ መምህርነት በሰርተፍኬት ተመርቄ በማገልገል ላይ እያለሁ ባገኘሁት የትምህርት ዕድል በጎንደር ዩኒቨርስቲ በእንግሊዘኛ ቋንቋ ትምህርት መስክ አጠናቅቄ በርዕሠ መምህርነት ያገለገልኩ ሲሆን መንግስት ለከፍተኛ ሃላፊነት በወረዳና በዞን ደረጃ በማገልገል ላይ እያለሁ ባገኘሁት የትምህርት ዕድል በድግሪ ፕሮግራም በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስት በኢጁኬሽናል ፕላኒንግና ማኔጅመንት ተመርቄያለሁ። በተመሳሳይ ከዚሁ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ የማስተርስ ፕሮግራም በደቨሎፕመንታል ሳይኮሎጂ ትምህርት መስክ አጠናቅቄያለሁ። በአጠቃላይ የሥራ ዘመኔ 10 ዓመት በመምህርነትና በርዕሠ መምህርነት ያገለገልኩ ሲሆን 20 ዓመት ደግሞ በተለያየ እርከን ከወረዳ፣ ዞን ያገለገልኩ ሲሆን አሁን ላይ ካለፉት አምስት ዓመት ጀምሮ በአማራ ክልል ህብረት ሥራ ማስፋፊያ ኮሚሽን በም/ኮሚሽነር ደረጃ እያገለገልኩ እገኛለሁ። በአመራርነት ዘመኔ የተለያዩ አጫጭርና መካከለኛ ደረጃ የአመራር ስልጠናዎችን የተካፈልኩ ሲሆን በርካታ የመካከለኛ አመራሮችን የማሰልጠን ዕድል በማግኘት ውጤታማ አስተዋፅኦ አበርክቻለሁ። በድርጅትና በመንግስት ሥራዎችም የተሰጠኝን ሃላፊነት በብቃት በመወጣት የምታወቅ ሲሆን በመጨረሻ የአመራር ምዘና ውጤቴም እጅግ በጣም ከፍተኛ ደረጃ ተሠጥቶኛል። በአጠቃላይ በሙያም ሆነ በአመራርነት ዘመኔ ምንም አይነት የዲስፕሊን ቅጣትም ሆነ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ የማላውቅ በከፍተኛ ትጋት ሃላፊነቴን በመወጣት ህዝቤን እያገለገልኩ እገኛለሁ።