ምክር ቤቱ በአንቀጽ 55፣ አንቀጽ 70(1)፣ አንቀጽ 79(4)(ሐ)፣ አንቀጽ 82(2)(ሐ)፣ አንቀጽ 101፣ አንቀጽ 102፣ አንቀጽ 103 እና... የተሰጡት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል።
የሕይወት ታሪክ
ስሜ ፌይሩዛ አብዱማሊክ ዳውድ ይባላል። ከአባቴ አብዱማሊክ ዳውድ እና ከእናቴ ሙኒራ ራሺድ ልጅ ሆኜ ሚያዝያ 3 ቀን 1999 ዓ.ም. በማያ ከተማ፣ አዋዳይ ክፍለ ከተማ፣ አዋዳይ 01 ቀበሌ ተወለድኩ።ባለትዳር ና የሁለት ልጆች እናት ነኝ
የትምህርት ጉዞዬን በዳንዲ ቦሩ መዋለ ህፆነት (KG) እና በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጀመርኩ። ከ9ኛ እስከ 10ኛ ክፍል በአዋዳይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተምሬያለሁ። ከ11ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ደግሞ በሐረማያ ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ተምሬ አጠናቀቅሁ። በመቀጠልም የመጀመሪያ ዲግሪዬን ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ አግኝቻለሁ።
የሥራ ልምዴን በአዋዳይ ከተማ ከ2014 ዓ.ም. ጀምሮ የተለያየ ጽፈት ቤት ሀላፊ ሆኜ አገልግያለሁ። በአሁኑ ጊዜም በማያ ከተማ የባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ኃላፊ ሆኜ እየሰራሁ እገኛለሁ።
በተጨማሪም የኦሮሚያ ክልል 6ኛ ዙር ጨፌ አባል በመሆን ሀገሬንና ሕዝቤን እያገለገልኩ እገኛለሁ።