የሕይወት ታሪክ

ዜና ማርቆስ ታደሰ በ1981 ዓ ም በአፋር ክልል በፈንታሌ ወረዳ ሳቡሬ ከተማ ተውለድኩ :: ዕድሜ ለትምህርት ሲደረሰ ከ1ኛ አሰከ 4ኛ ክፍል በሳቡሬ 1ኛ ደረጀ ት/ ቤት ተማርኩ::አባቴ የመንግስት ሰራተኛ በመሆኑ በስራ ዝወወር ወደ ደቡብ ክልል በመምጣቱ ከ5ኛ-6 ኛ ደንጋዉራ 1ኛ ደ/ት/ቤ/ት/ቤት 7ኛ-8ኛ ክፍል ሞርሲጦ 1ኛ/ደ/ት/ቤት 9ኛ-10ኛ ክፍል ሞርሲጦ 2ኛ/ደ/ት/ቤት ተምሬ የ10ኛ ክፍል ዉጤት ጥሩ በመሆኑ የ11ኛ-12ኛ ክፍልን በዋቸሞ 2ኛ/ደ/ት/ቤት ተምሬ የእንትራንስ ውጤት ጥሩ ስለ ነበር ከ1997-2000 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት (በእንግሊዝኛ ቋንቋ ማይነር) የመጀመሪያ ዲግሪየን አጠናቅቄ ከ2001-2002 ጌጃ2ኛ/ደ/ት/ቤት ከ2003-2014 ዓ ም ሞርሲጦ2ኛ/ደ/ት/ቤት ከ2015 እስከ አሁን ድረስ በየካቲት 25/67/2ኛ/ደ/ት/ቤት በአማርኛ ቋንቋ መምህርነት እያገለገልኩ አለሁ::ከ 2008-2011ዓ.ም በክረምት መርሃ ግብር በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ ድግሪዬን በ3.53 አጠናቅቄአለሁ::መ/ርት ዜና ባለ ትዳርና የሁለት ሴትና የሁለት ወንድ በአጠቃላይ የአራት ልጆች እናት ነኝ:: በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ተቋማት ውስጥ በከፍተኛ መምህርነት እና በክፍል ኃላፊነት እንዲሁም በትምህርት ክፍል (በዲፓርትመንት) አስተባባሪነት ከ2001 ዓ ም እሰከ 2018 ዓ ም በትምህርት መሪነት፣ በህዝብ ግንኙነት፣ እንዲሁም በማህበረሰብ እሴቶች ግንባታ ላይ አገልግያሌሁ ።