ምክር ቤቱ በአንቀጽ 55፣ አንቀጽ 70(1)፣ አንቀጽ 79(4)(ሐ)፣ አንቀጽ 82(2)(ሐ)፣ አንቀጽ 101፣ አንቀጽ 102፣ አንቀጽ 103 እና... የተሰጡት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል።
የሕይወት ታሪክ
ስሜ የሱፍ ሁሴን አደም ስሆን የተወለድኩት በአሰቦት ከተማ ሜኤሶ ወረዳ ጭሮ አውራጃ ምዕራብ ሐረርጌ ነው፡፡ የአንደኛ ደረጃ ትምህርቴን ከ1 እስከ 8 በአሰቦት የመጀመሪያ ደረጃ የተማርኩ ሲሆን 9ኛ ጭሮ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተምሬ ከ10ኛ እስከ 12ኛ ክፍል በጅግጅጋ ከተማ ሁለተኛ ደረጃ ተምሬ አጠናቅቄያለሁ፡፡ የከፍተኛ ትምህርቴን በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዲግሪ በማኔጅመንት በ2007 ዓ.ም የተመረቅኩ ሲሆን አሁንም በዚያው በጅግጅጋ ከተማ ትዳር መስርቼ የ12 ልጆች አባት ሆኜ እየኖርኩ እገኛለሁ፡፡ በአሁኑ ወቅት በ7ኛው ምርጫ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ሆኜ ተመርጫለሁ፡፡