የሕይወት ታሪክ

ስም አቶ ተመስገን ዘውዴ ንጋቴ እባላለሁ በአማራ ክልል በምስራቅ ጎጃም ዞን ሁለት እጁ እነሴ ወረዳ ሽሜ ቀበሌ ግንቦት 7 ቀን በ1978 ዓ.ም ከእናቴ ወይዘሮ ልንገርሽ ካሴ እና ከአባቴ አቶ ዘውዴ ንጋቴ ተወለድኩ እድሜየ ለትምህርት ሲደርስ ከርነዋሪ አጠቃላ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ካጠናቀቅኩ በኋላ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን በሞጣ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አጠናቅቄ በመምህርነት ሙያ ደብረ ማርቆስ መምህራን ኮሌጅ ተመርቄ በሁለት እጁ እነሴ ወረዳ ትምህርት ፅ/ቤት በመምህርነት እያገለገልኩ እያለ በነበረኝ ውጤታማነት በወረዳ አመራርነት ተመድቤ በተለያዩ የአመራር ርከኖች በአማካሪነት, በወረዳ አስተዳዳሪነት, በዞን መሬት መምሪያ ሃላፊነት, እንዲሁም በአሁኑ ሰዓት የሞጣ ከተማ ከንቲባ ሆኘ እያገለገልኩ ሲሆን በመምህርነት 3 አመት ,በአመራርነት ከ13 አመት በላይም አገልግያለሁ በስራ ላይ እያለሁ በነበረኝ ውጤታማነት በደብረ ማርቆስ ዩንቨርስቲ በመደበኛው መርሃ ግብር የመጀመሪያ ድግሪ በማኔጅመንት ሁለተኛ ድግሪ በቢዝነስ አድሚንስትሬሽን(MBA ) ተመርቄያለሁ :: => በነበረኝ የአመራርነት ቆይታም ልዩ ልዩ የቦርድ ተቋማትን በውጤታማነት መርቻለሁ :: በማህበራዊ ህይወትም ባለትዳር ነኝ :: ባለቤቴም በመጀመሪያ ድግሪ የማኔጅመንት ምሩቅ እና የመንግስት ሰራተኛ ነች :: ሁለት ወንድ ልጅ እና አንድ ሴት ልጅ ያሉኝ ሲሆን ከእኔ ጋር የማስተዳድራቸው የእኔ እና ባለቤቴ ደካማ እናት እና አባት እንዲሁም የማስተምራት እህት እና የወንድሜ ልጆች አሉኝ እንዲሁም ልጆቸን የምትንከባከብ የቤት ሰራተኛ ያለችኝ ሲሆን በአጠቃላይ 11 የቤሰብ አባላትን አስተዳድራለሁ :: በአጠቃላይ በስራ ዘመኔ ውጤታማ ፣በሰዎች ዘንድ ምስጉን እንዲሁም ሰውን የመርዳት እና የማስተባበር ችሎታ አለኝ :: =>በ7ኛው ዙር ሃገራዊ ምርጫም በተወዳደርኩበት ምርጫ ክልል 90% በላይ አብላጫ ድምፅ አግኝቸ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል በመሆኔ እጅግ ደስተኛ ነኝ :: በዚሁ እንደራሲ ተጨማሪ ሃላፊነት እና ተግባር ቢሰጠኝ ያለኝን ልምድ ተጠቅሜ በውጤታማነት ለማገልገል ዝግጁ መሆኔን በአክብሮት እገልፃለሁ :: አመሰግናለሁ !!