ምክር ቤቱ በአንቀጽ 55፣ አንቀጽ 70(1)፣ አንቀጽ 79(4)(ሐ)፣ አንቀጽ 82(2)(ሐ)፣ አንቀጽ 101፣ አንቀጽ 102፣ አንቀጽ 103 እና... የተሰጡት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል።
የምርጫ ክልል
ቃሉ 2
ክልል:
አማራ
በካርታው ላይ ለማየት ጠቅ ያድርጉ
የሕይወት ታሪክ
ስሜ ፋጡማ ይማም እብራሂም ከአባቴ ከሸይህ ይማም እብራሂም እና ከእናቴ ከአንሻ መሃመድ የሱፍ በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን በቃሉ ወረዳ በአብቾ 019 ቀበሌ ሃምሌ 11/972 ተወለድኩ እድሜየ ለትምህርት ሲደርስ በደጋን 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ከ1ኛ እስከ 6ኛ ክፍል ድረስ ተማርኩ ከዚያም 7ኛ እና 8ኛ ክፍልን በባቲ ከተማ የተማርኩ ሲሆን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት በኮምቦልቻ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ጨረስኩ፡፡ባለትዳር እና የ 3 ልጆች እናት ነኝ፡፡
የኮሌጅ ትምህርቴን በኮምቦልቻ ግብርና ኮሌጅ በተፈጥሮ ሃብት አያያዝ ተመርቄ በቃሉ ወረዳ በተለያዩ ቀበሌወች በተፈጥሮ ሃብት ባለሙያነት አገልግያለሁ
በደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር በቃሉ ወረዳ በተለያዩ የሃላፊነት ቦታወች በሹመት ህብረተሰቡን በቅንነትና በታማኝነት አገልግያለሁ ከዚያም የመጀመሪያ ድግሪየን ከባህርዳር ዩነቨርሲቲ በማኔጅመንት እና በተጨማሪም ከሃረማያ ዩኒቨርሲቲ በዲግሪ በናቹራል ሪሶርስ ማኔጅመንት ተመረኩ እንዲሁም የሁለተኛ ድግሪየን በጦሳ ኢኮኖሚክ ደቨሎፕመንት ኮሌጅ በጥሩ ውጤት አጠናቅቄያለሁ ፡፡
በኀላም በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ በኮምቦልቻ ቅርንጫፍ የደን ማኔጅመንትና አጠቃቀም የስራ ሂደት በመሆን በሹመት ለረጅም ግዜ አገልግየ በውጤታማነት አሳልፌያለሁ
ከዚያም በሌላ ሹመት የቃሉ ወረዳ የብልጽግና ጽ/ቤት ሃላፊ በመሆን ለትንሽ ግዜ ካገለገልኩኝ በኀላ የደቡብ ወሎ ዞን ኢንደስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊነት በሹመት ተሰጥቶኝ የተሸለ አፈጻጸም በማስመዝገብ ቆይቼ በሌላ ሃላፊነት የአማራ ብረታብረት ኢንደስትሪ የኮምቦልቻ የፋርም ኢምፕልመንት ፋብሪካ ምክትል ስራ አስኪያጅ የአስተዳደር፤የገበያና ሎጀስቲክስ ዘርፍን በአግባቡ እየመራሁ እገኛለሁ፡፡
በ6ኛው ሃገራዊ ምርጫም ለአማራ ክልል ም/ቤት የቃሉ ወረዳ ህዝብ ተወክየ በምክር ቤት አባልነት እና በቐሚ ኮሚቴ አባልነት ለአምስት አመታት በቅንነትና በብቃት ተወጥቻለሁ፡፡