የሕይወት ታሪክ

ስሜ አሚናት ሁሴን እብራሂም እባላለሁ፣ ሀምሌ 9/11/1979 ዓ.ም በአብክመ ኦሮሞ ብ/ሰብ አስተዳደር ዞን በባቲ ወረዳ ኤላ ቀበሌ ከአባቴ ሁሴን እብራሀሂም እና ከእናቴ ሉባባ አብዱ ተወለድኩ። የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቴን በመልካ ገላና አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ከ1ኛ-4ኛ ክፍል ተማርኩኝ፣ ከ5ኛ-8ኛ ክፍል በባቲ ከተማ 1ኛ ደረጃ ቁጥር አንድ ት/ቤት በመከታተል በ1994 የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስጄ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን በባቲ ቀይመስቀል 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በመከታተል በ1996 ዓ.ም 10ኛ ክፍል ቢሄራዊ ፈተናን በመውሰድ አጠናቀኩ። በ1997 ዓ.ም በደሴ መምህራን ት/ት ኮሌጅ በቋንቋ ዲፓርትመንት ለሶስት አመታት ተከታትየ ሰኔ 30/1999 በዲፕሎማ ተመረኩ። ሀምሌ 1/11/1999 ዓ.ም በመምህርነት ሙያ ተቀጥሬ እስከ መስከረም 18/2001 የማስተማር ስራ ሰራሁ። ከመስከረም 19/2001 ዓ.ም እስከ ህዳር 2006 ዓ.ም በአመራርነት በባቲ ወረዳ፣ደዌ ሀረዋ ወረዳና በደዋ ጨፋ ወረዳ በተለያዩ ሀላፊነቶች ሳገለግል ቆይቼ እራሴን በትምህርት ለማብቃት ድርጅቴ በሰጠኝ የትምህርት እድል በወሎ ዩንቨርሲቲ ከህዳር 2006 ዓ.ም እስከ ሰኔ 2008 ትምህርቴን በመከታተል በማናጅመንት ዲፓርትመንት የመጀመሪያ ድግሪዬን ሰኔ 23/2008 ዓ.ም ተመረኩ። ከጥቅምት 1/2/2009 ዓ.ም እስከ ሀምሌ 2010 ዓ.ም በደዋ ጨፋወረዳ የውሃ ፅ/ቤት ኋላፊ፣ እንዲሁም የብዓዴን ፅ/ቤት ሀላፊ በመሆን ህዝቤን በታማኝነት አገለገልኩ። ከሀምሌ 4/2010 ዓ.ም ጀምሮ በኦሮሞ ብ/ሰብ አስተዳደር ዞን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል (አደረጃጀት ዘርፍ ኋላፊ)በመሆን እስከ ጥቅምት 17/2012 ዓ.ም ኋላፊነቴን በአግባቡ በመወጣት አሁንም በድጋሜ እራሴን በትምህርት ለማብቃትና አቅሜን ለማሳደግ በሴቶች ሊግ (ክንፍ) በተሰጠኝ የትምህርት እድል በወሎ ዩንቨርሲቲ ከጥቅምት 2012 ዓ.ም እስከ ሀምሌ 2013 ዓ.ም የማስተርስ (ሁለተኛ) ድግሪዬን በፕሮጀክት ማናጅመንት ሀምሌ 2013 ዓ.ም ተመረኩ። ከትምህርት መልስ በቢሄረሰብ አስተዳደሩ ከጥቅምት 2014 ዓ.ም ዓ.ም ጀምሮ በአመራርነት በተለያዩ ተቋማት የዞን ም/አስተዳዳሪነትን ጨምሮ፣ ውሃና ኢነርጂ መምሪያ፣ እንዲሁም ገቢዎች መምሪያን በኋላፊነት እየመራሁ እገኛለሁ፡፡ በ2018 ዓ.ም በ7ኛ ዙር ሀገራዊ ምርጫ ፓርቲዬ ብልፅግና የህዝብን ዉክልናና አደራ በአግባቡ ትወጣለች ብሎ በማመን በባቲ ምርጫ ክልል ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት በእጩነት አቅርቦኝ በከፍተኛ ድምጽ አሸናፊ በመሆን ህዝቤ የሰጠኝን ዉክልናና አደራ በታማኝነትና በቁርጠኝነት ለመወጣት እንዲሁም በም/ቤቱ የሚሰጡኝን ተልኮዎች በውጤታማነት ለመወጣት በዝግጅት ላይ እገኛለሁ። አሚናት ሁሴን እብራሂም የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባል ነሀሴ 2018 ዓ.ም ባቲ