የሕይወት ታሪክ

አቶ ጉተማ ቢፍቱ ቦሩ በኦሮሚያ ክልል፣ በምሥራቅ ሸዋ ዞን፣ ቦሰት ወረዳ በገሪ ኑራሄራ ቀ/ገ/ማ ሰኔ 12 ቀን 1972 ዓ.ም ተወለዱ። አባታቸው አቶ ቢፍቱ ቦሩ ጂማ ሲሆኑ፣ እናታቸው ወይዘሮ ተሊሌ ዳዲ ሐዋስ ይባላሉ። አቶ ጉተማ በግብርናው ዘርፍ ሰፊ ዕውቀትና ክህሎት ያካበቱ ሲሆን፣ የትምህርት ዝግጅታቸውም የሚከተለውን ያካትታል፦ *የ1ኛ ደረጃ ትምህርታቸውነ በአለንጪቲ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ተከታትለዋል አንዲሁ 2ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በቦሰት 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የተከታተሉ ሲሆን * ዲፕሎማ በዕፅዋት ሳይንስ (Plant Science): በ1998 ዓ.ም ከሆለታ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ አጠናቀዋል። * የመጀመሪያ ዲግሪ (B.Sc.) በዕፅዋት ሳይንስ: ጥር 28 ቀን 2004 ዓ.ም ከአምቦ ዩኒቨርሲቲ ተመርቀዋል ። * የመጀመሪያ ዲግሪ (B.Sc.) በገጠር ልማትና ግብርና ስርፀት: ሰኔ 30 ቀን 2004 ዓ.ም ከሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በርቀት ትምህርት ፕሮግራም ተመርቀዋል ። በዕፅዋት ሳይንስና በገጠር ግብርና ልማት ያካበቱትን ዕውቀት በመጠቀም በግብርናው ዘርፍ አና በተለያዩ ቦታዋች በካበቱት ልመድና አውቀት በተለያዩ ቦታዋች ላይ በመመደብ ማህበረሰባቸውን እና ሀገራቸውን በታማኝነት እያገለገሉ ይገኛሉ።