ምክር ቤቱ በአንቀጽ 55፣ አንቀጽ 70(1)፣ አንቀጽ 79(4)(ሐ)፣ አንቀጽ 82(2)(ሐ)፣ አንቀጽ 101፣ አንቀጽ 102፣ አንቀጽ 103 እና... የተሰጡት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል።
የሕይወት ታሪክ
ዶ/ር ፋሩቅ አልይ ሙሳ 1976 ዓ.ም. ከአባቱ አቶ አልይ ሙሳ እና ከእናቱ ወ/ሮ ኑዛሃ አህምድ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት፣ ምዕራብ ሀረርጌ ዞን፣ ሃብሮ ወረዳ፣ በበልበሊቲ ቀበሌ ተወለደ።የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን (ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል) በበልበሊቲ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት (ከ1982 እስከ 1989 ዓ.ም.) የተከታተለ ሲሆን፣ በመቀጠልም በገለምሶ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመማር ትምህርቱን ከ1991 እስከ 1994 ዓ.ም. አጠናቅቋል።ዶር ፋሩቅ አልይ ሙሳ ከፍተኛ ትምህርቱን በመቀለ ዩኒቨርሲቲ በመከታተል በአንስሳት ህክምና (Doctor of Veterinary medicine) የመጀመሪያ ዲግሪውን በ2000 ዓ.ም. አግኝቷል። የሙያ ሥራውን የጀመረው በገመችስ ወረዳ የአንስሳት ና ኣሳ እርባታ ጽ/ቤት ሲሆን፣ ከ2001 እስከ 2002 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ውስጥ የግብርና ልማት ሥራዎችን ተግባራዊ በማድረግ ከገጠር ማኅበረሰቦች ጋር በቅርበት ሠርቷል። በተሰማራበት የሙያ መስክ ግንባር ቀደምና ለሌሎች አርአያ በመሆኑም በ2002 ዓ.ም. ወደ አመራርነት በመምጣት፣ በገመችስ ወረዳ የአንስሳት ና ኣሳ እርባታ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሆኖ እስከ 2003 ዓ.ም. አገልግሏል። በገመችስ ወረዳ ያበረከተው ውጤታማ አመራር ወደ ቦከ ወረዳ እንዲሸጋገር ያደረገው ሲሆን፣ ከ2003 እስከ 2005 ዓ.ም. የቦከ ወረዳ የግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ በመሆን ኃላፊነቱን ተወጥቷል። አንድሁም በምአሶ ወረዳ የአርብቶኣደር ጽ/ቤት ኃላፊ በመሆን ከ2005 እስከ 2006 ዓ.ም ሰርትዋል። በወረዳ ደረጃ ያበረከተው ውጤታማ አመራር ወደ ዞን ደረጃ እንዲሸጋገር ያደረገው ሲሆን፣ ከ2007 እስከ 2009 ዓ.ም. የምዕራብ ሀረርጌ ዞን የአርብቶኣደር ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ በመሆን አገልግለዋል፡፡ ያለውን ባለሙያነት ለማጠናከር ቁርጠኛ የሆነው ዶር ፋሩቅ አልይ፣ ወደ ሀረማያ ዩኒቨርሲቲ በመግባት በ2011 ዓ.ም. በእንስሳት መህበረሰብ ጤና (Masters in Veterinary Public health) የማስተርስ ዲግሪውን አግኝቷል። በመቀጠልም ከ2012 እስከ 2015 ዓ.ም የምዕራብ ሀረርጌ ዞን የግብርና ጽ/ቤት የእንስሳት ጤና ኢፒድሞሎጂ አከስፐርት በመሆን ሰርተዋል፡፡ዶ/ር ፋሩቅ አልይ ከ2016 እስከ 2018 ዓ.ም. ድረስ በምዕራብ ሀረርጌ ዞን የግብርና ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ ሆኖ ሠርቷል። ዶ/ር ፋሩቅ ከእንስሳ ህክምና ባለሙያነት አንስቶ በእያንዳንዱ የሕዝብ አገልግሎት ደረጃዎች ውስጥ ውጤታማ በመሆን ቁርጠኝነት አሳይቷል።