ምክር ቤቱ በአንቀጽ 55፣ አንቀጽ 70(1)፣ አንቀጽ 79(4)(ሐ)፣ አንቀጽ 82(2)(ሐ)፣ አንቀጽ 101፣ አንቀጽ 102፣ አንቀጽ 103 እና... የተሰጡት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል።
የሕይወት ታሪክ
መንደሬ ጌታሁን እባላለሁ የሁለት ልጆች እናት ነኝ ተወልጄ ያደኩት በከምባታ ዞን ዳምቦያ ወረዳ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ነኝ ።የአሁኑን የኃላፊነት ቦታ ከመያዘ በፊት የከምባታ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ሆኜ ለሶስትአመታት አገልግያለሁ ።ከዛም ባሻገር በዞን በተለያዩ መምሪያዎች እንዲሁም በከተማ እና በወረዳ በአመራሪነት አገልግያለሁ ።
በትምህርት ዝግጅት ረገድም በዴቬሎፕመንት ማኔጅሜንት ከሀዋሳ ዩኒቨርስቲ በሁለተኛ ዲግር ተመርቀያለሁ።
ተወልጄ ያደኩበትን ማህበረሰብ የማገልገል ከፍተኛ ፍላጎት ስለነበረኝ በ20ዎቹ የመጀመሪያ ዕድሜዬ
የዳምቦያ ወረዳ አመራር በመሆን ቀጥሎም የወረዳው ምክትል ዋና አስተዳዳሪና የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት ኃላፊ በመሆን አገልግያለሁ። በመቀጠልም በዞን ደረጃ ከመምሪያ ኃላፊነት አንስቶ አስተባባሪ ኮሚቴ በመሆን የሠራሁ ሲሆን አሁን ደግሞ በሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ በማሸነፍ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል እንድሆን በሕዝብ ተመርጫለሁ