ምክር ቤቱ በአንቀጽ 55፣ አንቀጽ 70(1)፣ አንቀጽ 79(4)(ሐ)፣ አንቀጽ 82(2)(ሐ)፣ አንቀጽ 101፣ አንቀጽ 102፣ አንቀጽ 103 እና... የተሰጡት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል።
የሕይወት ታሪክ
እኔ ወ/ሮ ፈንታነሽ አባተ ፈንታ በአማራ ክልል በምስራቅ ጎጃም ዞን በእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ በ03/04/1967 ዓ/ም የተወለድሁ ሲሆን በትምህርት ዘርፍ 1987ዓ/ም በአማርኛ ቋንቋ ባህርዳር ትምህርት ኮሌጅ በዲፕሎማ በኢትዮጵያ ቋንቋዎች እና ስነጽሁፍ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ1997ዓ/ም በዲግሪ እንዲሁም በስርዓተ ጾታ እና ልማት በባህርዳር ዪኒቨርሲቲ የማስተርስ ትምህርቴን በ2010 አጠናቅቂያለሁ፡፡
በስራ ልምድ ረገድ በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች ህዝቦች ክልላዊ መንግስት በመምህርነት በአማራ ክልል በምስራቅ ጎጃም ዞን በእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ በተለያዩ ጽ/ቤቶች የስርዓተ ጾታ ኤክስፐርት የሴቶች እና ወጣቶች ጉዳይ ጽ/ቤት ሃላፊ፣በገቢዎች ጽ/ቤት የግብር ትምህርት እና ኮሚኒኬሽን ባለሙያ እና አስተባባሪ፣የህዝብ ተሳትፎ አማካሪ ጽ/ቤት ሃላፊ፣ የምስራቅ ጎጃም ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ሃላፊ እና የከተማ እና መሰረተ ልማት መምሪያ የእቅድ በጀት ዝግጅትና ክትትል ግምገማ ባለሙያ በመሆን ከ01/11/1987ዓ/ም እስካሁን ድረስ እያገለገልሁ እገኛለሁ ፡፡በዚህ የስራ ዘመኔ ዉስጥ በሃላፊነት በታማኝነት እና በተግባራዊ ዉጤት በመንግስትም ይሁን በፓርቲ ተግባራት ንቁ ተሳትፎ አድርጌያለሁ፡፡
በቀጣይም እንደሀገር የሚጠበቅብኝን ሃላፊነት ለመወጣትና የወከለኝን ህዝብ መብት እና ጥቅም ለማስከበር ያላሰለሰ ጥረት ለማድረግ ዝግጁ መሆኔን በዚሁ አጋጣሚ ለመግለጽ እወዳለሁ፡፡