የሕይወት ታሪክ

ተረፈ በዳዳ ኢታንሳ ተረፈ በዳዳ እታንሳ ጥር 12ቀን 1976 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል ፣ በምዕራብ ሸዋ ዞን በጅባት ወረዳ በጋሞ አዳዲ ቀበሌ ተወለደ ። በመልካም ቤተሰብ ውስጥ በማደጉ ከልጅነቱ ጀምሮ አክብሮትን ፣ ኃላፊነት መውሰድን፣ ትብብርንና ሌሎችን ማገልገል የሕይወት እሴቶች አድርገው ወስደዋል። በትምህርቱ ዘርፍ በአካውንቲንግና ፋይናንስ እና በቢዝነስ ማናጅመንት የመጀመሪያ ዲግሪና እንዲሁም በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን /MBA/ የማስተርስ ዲግሪ አግኝቷል። በአሁኑ ወቅትም በሊደርሺፕ ዘርፍ የዶክትሬት ተማሪ ነው። ከመደበኛ ትምህርቱ በተጫማሪ የሙያ የእውቀቱና የአመራር አቅሙን ለማሳደግ በኢትዮጵያና በተለያዩ የውጭ አገራት በተካሄዱ ስልጠናዎች ተሳትፏል ።ከእነዚህ መካከል በቻይና፣ ቱርክዬ እና ሲንጋፖር የተካሄዱ ሥልጠናዎች ይገኙበታል። ተረፈ በአምቦ ዩኒቨርስቲ ሜዲካል ኮሌጅ የቦርድ አባል ሆኖ ያገለገለ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የእናት ባንክ የቦርድ አባል ፣ በባንኩ የሥጋትና የሕግና የደንብ ተገዢነት ንዑስ ኮሚቴ ምክትል ስብሳቢ፣ የግንባታ ንዑስ ኮሚቴ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል ። በተጫማሪም የሰላምና ዕድገት ተልዕኮ አገር በቀል ቻሪቲ የቦርድ ስብሳቢ ሆኖ እያገለገለ የሚገኝ መሆን በዚህ ኃላፊነቱም ሰላምና ማህበራዊ ልማትን ፣ የህብረተሰብ ተሳትፎን የሚያጠናክሩ ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል ። ተረፈ በትምህርት፣ በሙያ እና በአመራር ልምዱ ያገኘውን ዕውቅና ልምድ ለሰላምና ለልማት ለማበርከት ቁርጠኛ ነው።