የሕይወት ታሪክ

ወ/ሮ ሮዛ መሐመድ ሁስማን እባላለሁ ። ነሀሴ 18 ቄን 1981 ዓ ም በኦሮሚያ ክልል ኢሉባቦር ዞን ዱዲ ወረዳ ላሎ ከተማ ከአባቴ ከአቶ መሐመድ ሁሱማን እና ከእናቴ ከወ/ሮ ፍንታዬ አሰፍ ተወለድኩ። የአንደኛ ደረጃ ት/ት በላሎ ከተማ 1985_1992 የተማረኩ ስሆን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት በጎሬ ሁለተኛ ደረጃ ት/ት 1992_1995 አጠናቀቁ። የከፈተኛ ትምህርት ከባህር ዳር ዩኒቨርስቲ 1996_1998 (Food technology ) በተጨማሪ በኦሮሚያ እስቴት ዩኒቨርስቲ በማኔጅመንት የመጀመሪያ ድግሪ 2011-2013 በMBA ከሪፊት ቫሊ ዩኒቨርስቲ 2012-2014 እጠነቀቃለሁ ። የስራ ልማድ በተመለከተ በወረዳ ደረጃ የተለያዩ መስሪያ ቤቶች ሀላፊ እስከ የወረዳ ዋና አስተዳደር ሁኜ ሰርቻለሁ። በዞን ደረጃ እና በተለያዩ ከተሞችም በፓርቲ ሀላፊ አና በክ/ማ ዋና አስተዳደር አና በሁን ሰዓት የሸገር ከተማ ማዘጋጃ ማናጀር በመሆን ስራዬን በታማኝነት አና በቆራጥነት በተሰጠኝ ሀላፊነት ህዝቤን እያገለገልኩ እገኛለሁ ።