የሕይወት ታሪክ

የተከበሩ ወይዘሮ ፍቅርቴ አብርሃም መና የሕይወት ታርክ ወይዘሮ ፍቅርቴ አብርሃም መና ህዳር 23 ቀን 1982 ዓ.ም በአባታቸው በአቶ አብርሃም መና እና በእናታቸው በወይዘሮ ታመነች አንጁሎ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን ቦረዳ ወረዳ ሀምብሳ ቀበሌ ተወለዱ። ወይዘሮ ፍቅርቴ የትምህርት ህይወታቸውን በፅናትና በትጋት ያከናወኑ ሲሆን የትምህርት ደረጃቸውም የሚከተለው ነው፦ Ø  አንደኛ ደረጃ ትምህርት፡ እድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ በጋጋ ጎቾ ሙሉ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመግባት ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ተማሩ። Ø  ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት፡ በአካባቢው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ባለመኖሩ ምክንያት ከሀምብሳ ቀበሌ በ15 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ወደሚገኝ ዘፍኔ ከተማ በመመላለስ ከ9ኛ እስከ 10ኛ ክፍል ትምህርታቸውን አጠናቀቁ። Ø  ከ11ኛ ክፍል እስከ 12ኛ በአከባቢው የሁለተኛና መሰናዶ ደረጃ ትምህርት ቤት በአካባቢው ባለመኖሩ ምክንያት ከቦረዳ ወረዳ በ92 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ወደ ሚገኝ አርባ ምንጭ ከተማ በመሄድ በአርባምንጭ ሁለተኛና መሰናዶ ደረጃ ትምህርት ቤት ትምህርታቸውን አጠናቀቁ። Ø  የመጀመሪያ ዲግሪ (BA Degree)፡ በ2001 ዓ.ም ወደ አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ በመግባት በሶሽዮሎጂና ሶሻል አንትሮፖሎጂ ( Sociology and Social Anthropology) ሰኔ 2003 ዓ.ም ተመረቁ። Ø  ሁለተኛ ዲግሪ (MA Degree)፡ በፌዴራሊዝም እና አከባቢ ጥናት (Federalism and Local Government studies) ከኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በሐምሌ 2008 ዓ.ም ሁለተኛ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል። ወይዘሮ ፍቅርቱ ከተመረቁበት ጊዜ ጀምሮ በተለያዩ ደረጃዎች ህዝብና መንግስትን በትጋት አገልግለዋል፡፡ በዚህ መሰረት Ø  ከ01/12/2003 ዓ.ም. እስከ 10/12/2008 ዓ.ም. 3 ዓመት ከአንድ ወር በቦረዳ ወረዳ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት የሕዝብ ሥነ-ሕዝብ ጉዳዮች ማስተባበሪያ የሥራ ሂደት አስተባባሪ ሆነው አገልግለዋል። Ø  ከ12/01/2009 ዓ.ም. እስከ 29/02/2011 ዓ.ም. ድረስ ለ2 ዓመት ከአንድ ወር በቦረዳ ወረዳና ዘፊኔ ከተማ ማዘጋጃ ቤት የከተማ ነዋሪዎች ማህበረሰብ ተሳትፎ ማስተባበሪያ የሥራ ሂደት አስተባባሪ ሆነው አገልግለዋል። Ø  ከ29/02/2011 ዓ.ም. እስከ 16/11/2011 ዓ.ም. ድረስ ለ9 ወራት የቦረዳ ወረዳ ከተማ ልማትና ቤቶች ጽ/ቤት ኃላፊ ሆነው አገልግለዋል። Ø  ከ16/11/2011 ዓ.ም. እስከ 01/01/2013 ዓ.ም. ድረስ ለአንድ ዓመት ከአንድ ወር የጋሞ ዞን ከተማ ልማትና ግንባታ መምሪያ ምክትል ኃላፊ እና የመሬት ልማትና አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ ሆነው አገልግለዋል። Ø  ከ01/01/2013 ዓ.ም. እስከ 03/13/2015 ዓ.ም. ድረስ ለ3 ዓመት የጋሞ ዞን ሳይንስና ቴክኖሎጂ መምሪያ እና የጋሞ ዞን ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ሆነው አገልግለዋል። Ø  ከ03/13/2015 ዓ.ም. እስከ 03/13/2018 ዓ.ም. ድረስ ለ3 ዓመታት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት የንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ እና የንግድና የገበያ ልማት ዘርፍ ኃላፊ ሆነው አገልግለዋል። Ø  በአጠቃላይ፣ በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች በድምሩ 13 ዓመታት አገልለዋል። በአገልግሎት ዘመናቸው ጠንካራ የሥራ ሥነ-ምግባር፣ ትጋት፣ ቁርጠኝነትና ትጉህነት አሳይተዋል። Ø  የቤተሰብ ሁኔታ በሚመለከት ዕድሜያቸው ለትዳር ስደርስ ከባለቤታቸው ከአቶ አበሻ አሽኮ ቶጋ ጋር በጥር 11/2004 ዓ/ም ህጋዊ ጋቢቻ የመሰረቱ ሲሆን ባለትዳርና የልጆች እናት ናቸው፡፡ Ø  የቋንቋ ችሎታቸው የአማርኛ፣ የጋሞኛ፣ እና የእንግሊዝኛ ቋንቋዎችን በብቃት የመፃፍ፣ የማንበብ፣ የመናገርና የመስማት ችሎታ አላቸው። Ø  የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልነት፡ በ7ተኛው ዙር ሀገራዊና ክልላዊ ጠቅላላ ምርጫ በብርብር ምርጫ ክልል የምዕራብ አባያ ወረዳ፣ ብርብር ከተማ አስተዳዳር፣ ቦረዳ ወረዳና ዘፍኔ ከተማ አስተዳደር ህዝብን በመወከል በምርጫ ክልሉ ውስጥ ባሉት 106 ምርጫ ጣቢያዎች በሙሉ በወከሉት የግልጽግና ፖለቲካ ፓርቲ በከፍተኛ ድምፅ በማግኘት ተመርጠው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል በመሆን አገራቸውንና የወከለውን ህዝብ በማገልገል ላይ ይገኛሉ፡።