የሕይወት ታሪክ

የሕይወት ታሪክ እኔ አለውያ ጣሀር አደም እባላለሁ። የተወለድኩት በ1979 ዓ.ም በጎንደር ከተማ፣ አማራ ክልል፣ ኢትዮጵያ ነው። አሁንም በጎንደር ከተማ እኖራለሁ። ኢትዮጵያዊት ሲሆን በጾታ ሴት እና ያገባሁ ነኝ። እድሜየ ለትምህርት ሲደርስ ማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጭልጋ ወረዳ አይከል ኢለመንተሪ ት/ት ቤት እና የመሰናዶ ትምህርቴን ከዛው ጨረስኩ ተማርኩ በትምህርት ዘርፍ በ2001 ዓ.ም. ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ BSc በApplied Mathematics በCGPA 2.10/4.00 ተመርቄያለሁ። በ2013 ዓ.ም. ከራዳ ኮሌጅ BA በManagement በCGPA 3.35/4.00 አግኝቻለሁ። በ2016 ዓ.ም. ደግሞ ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ MBA በBusiness Administration በCGPA 3.50/4.00 ተመርቄያለሁ። በመሆኑም የትምህርት ዝግጅቴ በሂሳብ፣ በማኔጅመንት እና በቢዝነስ አስተዳደር የተጣመረ እውቀት እንዲኖረኝ አስችሎኛል። የሥራ ሕይወቴን በትምህርት እቅድና ዝግጅት ባለሙያነት ጀምሬያለሁ። ከ10/05/2002 እስከ 18/04/2006 ዓ.ም. በዚህ የሥራ መደብ በመሥራት የዕቅድ ዝግጅትና የሙያ ልምድ አግኝቻለሁ። ከ19/04/2006 እስከ 30/05/2010 ዓ.ም. የሴቶች ሊግ ኃላፊ በመሆን በሴቶች ጉዳይ፣ በአደረጃጀትና በአመራር ላይ ሠርቻለሁ። ከ01/06/2010 እስከ 11/05/2014 ዓ.ም. ደግሞ የሕዝብ ቅሬታ ሰሚ ኃላፊ በመሆን ከሕዝብ የሚቀርቡ ቅሬታዎችን በመቀበል፣ በመመርመርና ተገቢውን ምላሽ እንዲያገኙ በማስተባበር ሠርቻለሁ። ከ12/05/2014 እስከ 07/03/2015 ዓ.ም. የገቢዎች ጽህፈት ቤት ኃላፊ በመሆን የተቋሙን ሥራዎች በማስተባበርና በመምራት ኃላፊነቴን ተወጥቻለሁ። ከ03/05/2015 እስከ 30/02/2017 ዓ.ም. በትምህርት ላይ በመሥራት የማስተማርና የትምህርት ሥራ ልምድ አግኝቻለሁ። በመቀጠልም ከ01/04/2018 እስከ 04/01/2019 ዓ.ም. የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ በመሆን በድርጅታዊ አደረጃጀት፣ በአመራር፣ በዕቅድና በሥራ አፈጻጸም ክትትል ላይ ሠርቻለሁ። በአጠቃላይ 3 ዓመት የባለሙያነት ልምድ እና 10 ዓመት የአመራርና የማኔጅመንት ልምድ አለኝ። በዕቅድ ዝግጅት፣ በሰው ኃይል አመራር፣ በተቋማዊ አስተዳደር፣ በሕዝብ ቅሬታ አስተናጋጅነት፣ በሴቶች ጉዳይ እና በድርጅታዊ አደረጃጀት ዘርፎች የተለያየ የሥራ ልምድ አካብቻለሁ። ዋና የሙያ ፍላጎቴ ማኔጅመንትና አመራር ሲሆን፣ ያለኝን የትምህርት ዝግጅትና የሥራ ልምድ በመጠቀም በተቋማዊ አመራር፣ በሥራ አፈጻጸም ማሻሻል እና በሰው ኃይል ልማት ላይ የበለጠ አስተዋፅኦ ማድረግ እፈልጋለሁ። በቋንቋ ችሎታዬ አማርኛን በጣም ጥሩና ቀልጣፋ በሆነ መልኩ መናገርና መጻፍ እችላለሁ። እንግሊዝኛንም በጣም ጥሩ ደረጃ መናገርና መጻፍ እችላለሁ። በትምህርቴ፣ በሥራ ልምዴና በአመራር ችሎታዬ ላይ በመመስረት ለተሰጠኝ ኃላፊነት በትጋትና በተጠያቂነት ለመሥራት ዝግጁ ነኝ።