የሕይወት ታሪክ

ፍሬሕይወት ፍቃዱ ውቃው (ፒኤችዲ) ፍሬሕይወት ፍቃዱ (ፒኤችዲ) ከ12 ዓመታት በላይ በሚኒስቴር መስሪያቤት እና በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የፖሊሲ አማካሪ እና የህዝብ ግንኙነት አመራር እንዲሁም ባለሙያ ናቸው። ከነሐሴ 2017 ዓ.ም ጀምሮ በማዕድን ሚኒስቴር የሚኒስትሩ አማካሪ ሆነው እያገለገሉ ይገኛሉ። በዚህ ኃላፊነታቸው፣ ሚኒስትሩን በለውጥ አምጪ የህዝብ ፖሊሲ ላይ ያማክራሉ፣ አጠቃላይ የልማት ስትራቴጂን እንዲቀረጽ ያስተባብራሉ፣ የማዕድን ዘርፍ የመንግስት አስተዳደር እና የማሻሻያ ሪፎርም ስራዎችን ይመራሉ። ፍሬሕይወት ፍቃዱ (ፒኤችዲ) ከቤይጂንግ ኖርማል ዩኒቨርሲቲ (በቻይና ሀገር) በኮምፓራቲቭ ኢዱኬሽን (የትምህርት ፖሊሲ እና አመራር) የፒኤችዲ ዲግሪ ያገኙ ሲሆን፣ የሶስተኛ ዲግሪ ጥናታዊ ፅሁፋቸው በኢትዮጵያ ዘላቂ የማዕድን ኢንዱስትሪ ውስጥ የከፍተኛ ትምህርት ተመራቂዎችን የስራ ስምሪት አቅም በማጠናከር ላይ ያተኮረ ነበር። እንዲሁም ከአምቦ ዩኒቨርሲቲ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ማስተማሪያ (TEFL) ማስተርስ ዲግሪ እና ከአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የእንግሊዝኛ ቋንቋ የመጀመሪያ ዲግሪ አግኝቷል። ፍሬሕይወት ፍቃዱ (ፒኤችዲ) ከዚህ ቀደም በማዕድን ሚኒስቴር የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ሆነው ያገለገሉ ሲሆን፣ የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ በመሆን የኮሙኒኬሽን ስትራቴጂ አዘጋጅተዋል፣ ግንዛቤ ፈጥረዋል፣ የሚዲያ ግንኙነቶችን መርተዋል፣ እንዲሁም የማዕድን ኢንቨስትመንት ፕሮግራሞችን አስተዋውቀዋል። ከ2008 እስከ 2012 በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ እና በአምቦ ዩኒቨርሲቲ በመምህርነት እና በተመራማሪነት አገልግለዋል። ተማሪዎችን በማስተማር፣ በማማከር እንዲሁም ለስራ አገልግሎት ማዕከል (Career Services Centre) በማስተባበር አገልግለዋል። ፍሬሕይወት ፍቃዱ (ፒኤችዲ) የማዕድን ዘርፍ የልማት እና ፖሊሲ፣ ስትራቴጂያዊ ዕቅድ፣ የህዝብ ፖሊሲ፣ ከፍተኛ ትምህርት እና የህዝብ አስተዳደር ላይ ሙያዊ ፍላጎቶች አሏቸው። የምርምር ፍላጎቶቻቸው ደግሞ የማዕድን ዘርፍ አስተዳደር፣ የከፍተኛ ትምህርት ፖሊሲ፣ የስራ ስምሪት እና የድህረ ምረቃ ጥናቶች ናቸው። አፋን ኦሮሞ እና አማርኛ ቋንቋ የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ሲሆን፣ በእንግሊዝኛ ቋንቋም ብቃት አላቸው። ፍሬሕይወት ፍቃዱ (ፒኤችዲ) ለስራቸው ከፍተኛ ፍቅር እና ተነሳሽነት ያላቸው ሲሆን ለማህበረሰብም ሆነ ሀገር አስተዋፅኦን ለማበርከት ይተጋሉ። ባለትዳር እና የሁለት ወንድ ልጆች እናትም ናቸው። ባለቤታቸው እና ልጆቻቸው በስራ እና በትምህርት ጉዞዋቸው ውስጥ ትልቁ አስተዋጽኦ አበርክተዋል።