ምክር ቤቱ በአንቀጽ 55፣ አንቀጽ 70(1)፣ አንቀጽ 79(4)(ሐ)፣ አንቀጽ 82(2)(ሐ)፣ አንቀጽ 101፣ አንቀጽ 102፣ አንቀጽ 103 እና... የተሰጡት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል።
የሕይወት ታሪክ
ስሜ ሀብቴ ፊታሞ አርፊጮ ይባላል። የተወለድኩት ከአባቴ ፊታሞ አርፊጮ እና ከእናቴ ቦጋለች ሰላቶ ቀን
ሐምሌ/ 0 6 / 1 9 7 0 ዓ.ም ላይ ነው። የተወለድኩትም በኦሮሚያ ክልል፣ በምስራቅ ሸዋ ዞን፣
በአዳማ-ቦሰት አካባቢ፣ በወንጂ-ሸዋ አለም ጤና ቀበሌ ነው። ያደግኩበት የቤተሰብ አስተዳደግና የአካባቢው ሁኔታ
ባህሪዬን፣ እሴቶቼን እና ስለ ሕይወት ያለኝን አመለካከት በመቅረጽ አስፈላጊ ሚና ተጫውተዋል።
የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቴን በወንጂሸዋ አለም ጤና ሚሽን ትምህርት ቤት ጀመርኩ። ከ 1973 ዓ.ም እስከ
1980 ዓ.ም ድረስ በዚያ ተምሬያለሁ። የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቴን ከጨረስኩ በኋላ፣ ወንጂ ሁለተኛ ደረጃ
ትምህርት ቤት ከ 1981 ዓ.ም እስከ 1 9 8 4 ዓ.ም ድረስ ትምህርቴን
ቀጠልኩ። እነዚህ የትምህርት የመጀመሪያ ዓመታት ዕውቀቴንና ክህሎቴን ለማሳደግ የሚያስፈልገኝን ጠንካራ መሠረት
ገንብተውልኛል።
በኋላም የሁለተኛ ዙር የኢትዮጵያ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና ማትሪክ ወሰድኩ። በ
1989/1990 ዓ.ም ውጤቴን ካሻሻልኩ በኋላ፣ ቀድሞ የገበሬዎች ማሰልጠኛ ተቋም ተብሎ
በሚጠራው አጋርፋ የግብርና ኮሌጅ ገብቼ ጠቅላላ ግብርና ተማርኩ። ስልጠናዬንም በተሳካ ሁኔታ አጠናቅቄያለሁ። ይህ
የግብርና ትምህርቴ ተግባራዊ ዕውቀት እንዳገኝ ከማድረጉም በላይ፣ በግብርና ልማት በኩል ማህበረሰብን ለማገልገል ያለኝን
ፍላጎት አጠናክሮልኛል።
በ 1999 ዓ.ም ወደ አላጌ የግብርና ኮሌጅ በመግባት የእንስሳት ጤና ትምህርቴን ቀጠልኩ። በ 2001 ዓ.ም
ትምህርቴን በማጠናቀቅ ረዳት የእንስሳት ሕክምና ባለሙያ በመሆን ተመረቅሁ። በእንስሳት ጤና ያገኘሁት ስልጠና
ተጨማሪ ተግባራዊና ቴክኒካዊ ዕውቀት እንዳገኝ አስችሎኛል፤ በግብርናና በእንስሳት ሀብት ዘርፍም አስተዋጽኦ
ለማድረግ አቅሜን አሳድጎልኛል።
የትምህርት ጉዞዬን በመቀጠል በቅድስት ማርያም ዩኒቨርሲቲ የግብርና ኢኮኖሚክስ ትምህርት ተምሬ በ 2005
ዓ.ም የመጀመሪያ ዲግሪዬን አገኘሁ። በመቀጠልም በ2008 ዓ.ም በሌላ የትምህርት መስክ ማለትም በእንስሳት
ጤና ዘረፍ ወደ ዲላ ዩኒቨርሲቲ በመግባት ትምህርቴን
በ 2013 ዓ.ም የ ዲግሪ ትምህርቴን በማጠናቀቅ ተመረቅሁ። ክዚህም በተጨማሪ በማኔጅመንት እና በፖለቲካ
ጉዳዮች በየጊዜው ወቅታዊ የሆኑ አጫጭር ስልጠናዎችን ወስጃለሁኝ። ሙያዊ ዕውቀቴን በተከታታይ እንዳሳድግና
ሰዎችን ለማገልገል እና ለልማት አስተዋጽኦ ለማድረግ ያለኝን አቅም እንዳሻሽል አስችሎኛል።
ከዲላ ዩኒቨርሲቲ ትምህርቴን ከጨረስኩ በኋላ በግብርና ዘርፍ አገልግያለሁ። ከ 2013 ዓ.ም እስከ
2018 ዓ.ም ባለሁብት ወረዳ ግብርና ጽቤት በመስራት፣ በወረዳው ከሚገኙ ቀበሌዎች በአንዱ ተመድቤ
አገልግያለሁ።
በዚህ ወቅት ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በቀጥታ በመስራት፣ በግብርና ሥራዎችና በገጠር ልማት ጉዳዮች ላይ የሥራ
ልምድ አግኝቻለሁ። ሥራዬ አርሶ አደሮች የሚያጋጥሟቸውን ችግሮችና በመሠረታዊ ደረጃ ተገቢውን የግብርና ድጋፍና
አገልግሎት መስጠት ያለውን ጠቀሜታ በተግባር እንድረዳ አስችሎኛል