የሕይወት ታሪክ

እኔ አለምነሽ ብርሃኑ ኦብሳ ከአባቴ ከአቶ ብርሃኑ ኦብሳ ከእናቴ ከወ/ሮ አታለለች አቶምሳ በኦሮሚያ ክልል በቡኖ በደሌ ዞን በዴጋ ወረዳ በዴጋ ቀበሌ 01 በ 01/05/1976 ዓ.ም ተወለድኩ። እድሜዬ ለትምህርት ሲደርስ 1ኛ ደረጃ ትምህርት በዴጋ መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፣ 2ኛ ደረጃ ትምህርት በበደሌ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተማርኩ ሲሆን የ12ኛ ክፍል ካጠናቀቁ ቦኋላ በ1996 ዓ.ም ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ገብቼ በአፕላይድ ኬሚስትሪ በመጀመሪያ ድግሪ ተመረኩ። ከዝያ በዴጋ ነገያ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመምህርነት ለሁለት አመት ከአገለገልኩ ቦኋላ በዴጋ ወረዳ በተለያዩ ጽህፈት ቤት በአመራርነት እና በባለሙያ ሳገለግል ነበር። በ4ኛ ዙር ምርጫ ዘመን በጮራ ዴጋ ምርጫ ክልል በመመረጥ የጨፌ አባልና የኢንዱስትሪ እና ከተማ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባል ሆኜም አገልግያለሁ። በ2009 ዓ.ም 2ኛ ድግሪ (MA) ለመማር የኢትዮጵያ ፓብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ገብቼ በ2010 ዓ.ም በአመራርነት እና መልካም አስተዳደር የትምህርት አይነት ተማረኩ ።በቡኖ በደሌ ዞንም በተለያዩ ተቋማት ላይ በአመራርነት እያገለገልኩ ነበር ። ከዝያ ቦኋላ ጮራ ዴጋ ምርጫ ክልል በመመረጥ የ6ኛ ዙር የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል እና የንግድ እና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባል ሆኜ እያገለገልኩ እገኛለሁ። በ7ኛ ዙር የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል በመሆን በድጋሚ እንዳገለግል ተመርጫለሁ። እኔ አሁን ባለ ትዳር እና የ2 ሴት እና 1ወንድ ልጆች እናት ነኝ።