የሕይወት ታሪክ

አቶ ጋሻው ዳኘው ላቀው እባላለሁ።በአማራ ክልል በደቡብ ጎንደር ዞን በሰዴ ሙጃ ወረዳ በ1979 ዓ.ም መጋቢት 21 ተወለድኩ።እድሜየ ለትምህርት ሲደርስ በ1984 ዓ.ም 1ኛ ክፍል የገባሁ ሲሆን የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቴን በሰዴ ሙጃ ወረዳ በአዳዳ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት አጠናቀኩ።የ2ኛ ደረጃ ትምህርቴን በስማዳ ወረዳ ታገል 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማርኩ።የመጀመሪያ ድግሪየን በመቀሌ ዩንቨርስቲ በጀርናሊዝምና ኮሙኒኬሽን የተማርኩ ሲሆን ሁለተኛ ድግሪየን በባህዳር ዩንቨርሲቲ በሚዲያና ኮሙኒኪሽን ተመርቂያለሁ።እንድሁም በአዲስ አበባ ከሚገኘው ናሽናል ኮሌጅ በቢዝነስ አስተዳደር ሁለተኛ ድግሪየን ተመርቂያለሁ። መስከረም 1/2000 ዓ.ም በስማዳ ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ኃላፊ ሆኜ ስራ የጀመርኩ ሲሆን ከ2002 እስከ 2004 ዓ/ም የመንግስት ኮሙኒኬሽን ኃላፊ ሆኜ ሰርቻለሁ።ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 2007 መጋቢት ድረስ በዚሁ ወረዳ የወረዳው አስተዳደር የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ፣ከ2008_2010 የደቡብ ጎንደር ዞን የወጣቶች አማካሪ፣በ2013 የደቡብ ጎንደር ዞን ምክትል ህዝብ ግንኙነት አማካሪና የዞኑ ኮሙኒኬሽን ኃላፊ እንድሁም ከ2014 _2018 መጨረሻ ድረስ የ6ኛው ዙር የፓርላማ አባል በመሆን ሰርቻለሁ።