የሕይወት ታሪክ

ክቡር አቶ ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር በክልላዊ..፣በሀገራዊና በአህጉር ደረጃ በንግድ ማህበራት አመራር፣ በማህበረሰብ አገልግሎት፣ በስፖርት አስተዳደር እና በብሔራዊ የግሉ ዘርፍ አመራር ዘርፎች ሰፊና ተከታታይ የአመራር ልምድ ያካበቱ ናቸው። የሙያ ጉዞያቸው ከቦርድ ደረጃ ኃላፊነቶችና ከማህበረሰብ ተሳትፎ በመነሳት፣ በክልላዊ፣ በብሔራዊ እና በአህጉር የንግድ ተቋማት ውስጥ ወደ ከፍተኛ የአመራር ኃላፊነት የተሸጋገረ ቀጣይነት ያለው የሙያ እድገትን ያሳያል። 2. የአሁኑ የአመራር ኃላፊነቶች 1. ፕሬዚዳንት | የኢትዮጵያ የንግድ ምክር ቤትና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት (ECCSA) የኢትዮጵያን የግሉ ዘርፍ ጥቅም በመወከል፣ የንግድ አካባቢን ለማሻሻልና የንግድ ማህበራትን ተቋማዊ አቅም ለማጠናከር የሚያስችል ከፍተኛ የአመራር ሚና እየተወጡ ይገኛሉ 2. ፕሬዚዳንት | የኦሮሚያ የንግድ ምክር ቤትና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት በኦሮሚያ ክልል የግሉ ዘርፍን በመወከል፣ የንግድ እና የኢንቨስትመንት እድሎችን ለማስፋፋትና የንግድ ማህበረሰቡን ተሳትፎ ለማጠናከር በከፍተኛ የኃላፊነት መንፈስ እየሠሩ ይገኛሉ። 3. የሥራ አስፈጻሚ አባል | የፓን-አፍሪካ የንግድ ምክር ቤትና ኢንዱስትሪ በአህጉራዊ ደረጃ የንግድ ትስስርን፣ የግሉ ዘርፍ ትብብርን እና የአፍሪካ የንግድ ግንኙነትን ለማጠናከር በሚደረጉ ጥረቶች የበኩላቸውን ሚና እየተወጡ ነው። በአጠቃላይ በክልላዊ፣ በብሔራዊ፣በአህጉራዊ እና በዓለም አቀፍ የንግድ መድረኮች የኢትዮጵያን የግሉ ዘርፍ ድምፅ በማጠናከር፣ የንግድ ትብብርን በማስፋፋት እና ለንግድና ኢንቨስትመንት ምቹ የሆነ አካባቢን ለማስፋፋት ከከፍተኛ ተነሣሽነት መንፈስ የተሰጣቸውን ኃላፊነት እየተወጡ ይገኛሉ።