የሕይወት ታሪክ

የሕይወት ታሪክ — በአማርኛ የግል መረጃ ሙሉ ስም፡- ተዋቸው አበበ ይመር የትውልድ ቦታ፡- የአማራ ክልል፣ ሰሜን ጎጃም ዞን፣ ሰሜን ሜጫ ወረዳ፣ መርዓዊ ከተማ፣ ብራቃት ቀበሌ የትውልድ ቀን፡- ህዳር 12 ቀን 1979 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ. ኖቬምበር 21 ቀን 1986) የሕይወትና የትምህርት ጉዞ እኔ በአማራ ክልል፣ በሰሜን ጎጃም ዞን፣ በሰሜን ሜጫ ወረዳ፣ (መርዓዊ ከተማ) ብራቃት ቀበሌ ፤ህዳር 12 ቀን 1979 ዓ.ም. ተወለድሁ፡፡ ከልጅነቴ ጀምሮ ለትምህርት፣ ለሥራና ለማኅበረሰብ አገልግሎት ትልቅ ፍላጎት በማዳበር የትምህርት ጉዞየን በትጋት ቀጥያለሁ። የኢለመንታሪ እና ሰከንዳሪ ትምህረቴን ካጠናቀቅሁ በኃላ በግብርና ሳይንስ ዘርፍ፣ በተፈጥሮ ሃብት ልማት የዲፕሎማ ትምህርቴን በማጠናቀቅ ነሐሴ 23 ቀን 1996 ዓ.ም. (Augest 29 2004) ተመረቅሁ። ይህንን ትምህርት ተከትሎም ወይም በተማርሁበት ሙያ ዘርፍ መሰረትም በ1997 ዓ.ም በግብርና ሙያተኝነት የሥራ ዓለምን ተቀላቀልሁ። በተግባር የሥራ ልምዴን እያዳበርሁ በተመሳሳይ ጊዜ ትምህርቴን በማሻሻል በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በግብርና ሳይንስ፣ በተፈጥሮ ሃብት ዘርፍ የመጀመሪያ ዲግሪየን ጥቅምት 20 /2004 ዓ.ም (31 Octomber 2011) አግኝቻለሁ። ከዚያም በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በግብርና ሳይንስ፣ በገጠር ልማት (Rural Development) የሁለተኛ ዲግሪየን ሰኔ 22 ቀን 2008 ዓ.ም (29 June 2016) ተመረቅሁ። ይህ የትምህርት ጉዞ ከዲፕሎማ ወደ የመጀመሪያ ዲግሪ፣ ከዚያም ወደ ሁለተኛ ዲግሪ የደረሰ ሲሆን፣ የእኔን የመማር ፍላጎት፣ ትጋትና ራስን የማሻሻል ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው። 3. የሥራ ታሪክ እኔ ከመስከረም 1 ቀን 1997 ዓ.ም. ጀምሮ በመንግሥት ሥራ በመሰማራት ለረጅም ዓመታት በተለያዩ የሙያና የአመራር ኃላፊነቶች ሕዝብንና መንግሥትን አገልግያለሁ። 3.1 በሰሜን ሜጫ ወረዳ የመጀመሪያ የሥራ ልምዴ በሰሜን ሜጫ ወረዳ በተፈጥሮ ሃብት ባለሙያነትና በግብርና ሱፐርቫይዘርነት በመሥራት ጀምርሁ። በዚህ የሥራ ዘመን የግብርና ምርታማነትን፣ የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃንና ዘላቂ የገጠር ልማትን ለማሳደግ በሚደረጉ ሥራዎች በንቃት ተሳትፌአለሁ። 3.2 የመርዓዊ ከተማ የውሃ አገልግሎት በቀጣይም በመርዓዊ ከተማ የውሃ አገልግሎት ሥራ አስኪያጅ ሁኘ በመሥራት ለከተማው ሕዝብ የውሃ አገልግሎት አቅርቦትና አስተዳደር የሚመለከቱ ኃላፊነቶችን ተወጥቻለሁ። 3.3 በአማራ ክልል ግብርና ቢሮ በአማራ ክልል ግብርና ቢሮ በቆጋ መስኖ ልማት ፕሮጀክት ጽ/ቤት ከፍተኛ ባለሙያና በሥራ አስኪያጅነት በመሥራት የመስኖ ልማትንና የግብርና ልማትን በማስፋፋት ላይ አስተዋጽኦ አድርጌአለሁ። በተጨማሪም ከግብርና ጋር በተያያዙ የተለያዩ ፕሮጀክቶች የ "Focal Person" በመሆን የፕሮጀክቶችን ቅንጅት፣ አፈጻጸምና ክትትል በማስተባበር ሰርቻለሁ። ከመስከረም 1 ቀን 1997 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 1 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ባለው የሥራ ዘመኔ በቅንነት፣ በታማኝነት፣ በትጋትና በውጤታማነት በመሥራት የተሰጠኝን ኃላፊነት በተገቢው ሁኔታ ለመወጣት ጥረት አድርጌአለሁ። 4. የሕዝብ ተወካይነትና የፓርላማ ሥራ ከጥቅምት 1 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ በኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል በመሆን አዲስ የሕዝብ አገልግሎት ምዕራፍን ጀመርሁ። በስድስተኛው ዙር የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባል ሥር በሚገኝ ንዑስ ኮሚቴ የአመራር ኃላፊነት በመያዝ ሰርቻለሁ።በዚህ ኃላፊነት የግብርና አዋጆችን በደንብ በመመርመር እና እንዲጸድቁ በማድረግ ፖሊሲዎችን፣ የግብርና ልማት ሥራዎችን፣ የገጠር ልማትን፣ የመስኖ ልማትንና ከግብርና ዘርፍ ጋር የተያያዙ የሕዝብ ጉዳዮችን በመከታተል፣ በመገምገምና በማስተባበር የበኩሌን አስተዋጽኦ አበርክቻለሁ። በሰባተኛው ዙርም የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ሆነው የሕዝብን ጥያቄና ፍላጎት በመወከል የሕግ አውጭነት፣ የቁጥጥርና የውክልና ኃላፊነቶችን ለመወጣት ቀጥያለሁ። 5. የፖለቲካና የማኅበራዊ አመራር ልምድ ከፓርላማ ኃላፊነቴ በተጨማሪ በፓርቲው የቤተሰብ አደረጃጀትና በፖለቲካ ዘርፍ የአመራር ኃላፊነት በመያዝ ለአምስት ዓመታት ያህል አገልግያለሁ። ይህ ልምድ በሕዝብ አደረጃጀት፣ በአመራር፣ በቡድን ሥራ፣ በሕዝብ ተሳትፎና በተቋማዊ ቅንጅት የተግባር ልምዴን የበለጠ እንዳብር አስችሎኛል። 6. የሙያ ስኬቶችና አስተዋጽኦ ከመንግሥት ሥራ ከተቀላቀልሁበት ጊዜ ጀምሮ ለሕዝብ አገልግሎት በቅንነት፣ በታማኝነት፣ በትጋትና በተጠያቂነት በመሥራት የምታወቅ የሙያ ባለሙያና አመራር ነኝ።በተለያዩ የሥራ ዘመናት የተሰጠኝን ኃላፊነት በውጤታማነት በመወጣቴ የተለያዩ ማበረታቻዎችና እውቅናዎች ተሰጠውኛል። ከተሰጡኝ እውቅናዎች መካከል፤ ከዲፕሎማ ወደ የመጀመሪያ ዲግሪ የትምህርት ዕድል፤ ከመጀመሪያ ዲግሪ ወደ ሁለተኛ ዲግሪ የትምህርት ዕድል፤ የሜዳሊያ ሽልማቶች፤ የምስክር ወረቀቶች፤ የገንዘብ ሽልማቶች፤እንዲሁም በአይነት የተሰጡ ሌሎች የማበረታቻ ሽልማቶች ይገኙበታል።በተለይም በሥራ ውጤታማነት ምክንያት መንግሥት የትምህርት ዕድል በመስጠት በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ እስከ ሁለተኛ ዲግሪ ድረስ ተምሬ እንድጨርስ መደረጉ ከሙያ ሕይወቴ ዋና ዋና ስኬቶች አንዱ ነው። 7.የአመራር ፍልስፍናና የሥራ እሴቶች የእኔ የሥራ ሕይወት በትምህርት፣ በሙያ፣ በሕዝብ አገልግሎትና በአመራር የተገነባ ነው።የሥራ እሴቶቸ በተለይም፦ ቅንነት፣ ታማኝነት፣ ትጋት፣ ተጠያቂነት፣ ሕዝብን ማገልገል፣ ውጤታማነት፣ ተማሪነትና ራስን በቀጣይነት ማሻሻል ናቸው።ከቴክኒካዊ የግብርና ሙያ ወደ የአመራርና የሕዝብ ውክልና ሥራ ያደረግሁት ጉዞ የሙያ ብቃትንና የአመራር ልምድን በአንድ ላይ ያጣመረ ነው። 8. የወደፊት ራዕይ /Future Vision/ እኔ የተማርሁበትን ዕውቀት፣ያካበትሁትን የሙያ ልምድና የአመራር ተሞክሮ በመጠቀም ለሕዝብና ለሀገር የበለጠ አስተዋጽኦ ማድረግን እንደ ዋና የሕይወት ዓላማ እመለከታለሁ።በተለይም በግብርና፣ በገጠር ልማት፣ በተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ፣ በመስኖ ልማትና በሕዝብ ተሳትፎ የተገነባውን ሰፊ የሙያ ልምድ በሕግ አውጭነትና በሕዝብ ውክልና ሥራ በማጣመር የሀገር ልማትን ለማገዝ ቁርጠኛ ነኝ።