የሕይወት ታሪክ

እኔ የተከበሩ ወ/ሮ የመንግስት ፀጋው ዋለልኝ በ05/03/1987 የተወለድኩ ሲሆን፣ በማኔጅመንት የመጀመሪያ ዲግሪና በProject Planning and Management የማስተርስ ዲግሪ ያለኝና ሙያተኛና ልምድ ያካበትኩ አመራር ነኝ። በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልነት በማገልገል፣ በከተማ መሠረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ አባል በመሆን፣ እንዲሁም በአማራ ክልል በተለያዩ የአመራር ኃላፊነቶች ላይ በመስራት ሰፊ የሕዝብ አገልግሎት፣ የአመራርና የአስተዳደር ልምድ አካብቻለሁ። ከዚህም በተጨማሪ በአማራ ብልጽግና ቅርንጫፍ ዋና ጽ/ቤት የዓለም አቀፍ ግንኙነት ም/ዘርፍ ኃላፊ በቢሮ ኃላፊ ደረጃ እና በአማራ ክልል የመረጃና የአደረጃጀት አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ በመሆን አገልግያለሁ። በሥራ ዘመኔ የሥራ ዲሲፕሊንን፣ ታማኝነትን፣ ትጋትን፣ ብቃትንና ኃላፊነትን በተግባር ያሳየሁ አመራር በመሆኔ ከፍተኛ የኃላፊነት ደረጃ ላይ ባሉ አመራሮች አዎንታዊ ምስክርነት አግኝቻለሁ። ትዕግስት፣ ፅናት፣ ታማኝነት፣ ፈርሃ እግዚአብሔርና ለሕዝብ አደራ ታማኝ መሆን የአመራር መርሆዎቼ ናቸው። በያዝኩት እውቀት፣ ልምድና ሙያዊ ብቃት ለሕዝብና ለአገር የሚጠቅም ሥራ ለመስራት፣ የተሰጠኝንም የሕዝብ አደራ በሙሉ ኃላፊነትና በህሊና ለመወጣት የታቀዱ ናቸው። “የተሰጠኝን የሕዝብ አደራ በታማኝነት፣ በብቃትና በህሊና መወጣት የአመራር ዋና መርሄ ነው።”