ምክር ቤቱ በአንቀጽ 55፣ አንቀጽ 70(1)፣ አንቀጽ 79(4)(ሐ)፣ አንቀጽ 82(2)(ሐ)፣ አንቀጽ 101፣ አንቀጽ 102፣ አንቀጽ 103 እና... የተሰጡት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል።
የሕይወት ታሪክ
የግል ታሪክ
ስሜ ተስፋሁን ስመኝ ከበደ ይባላል። የተወለድኩት በአማራ ክልል፣በማዕከላዊ ጎንደር ፤በጎንደር ዙሪያ ወረዳ በማክሰኝት ከተማ የተወለድኩበት ዓ.ም 28/1/1974 በንግድ ስራ ከሚሰሩ ቤተሰብ ነው። የልጅነት ዘመኔን በማክሰኝት ከተማ አሳልፌያለሁ። ከልጅነቴ ጀምሮ ትምህርትን፣ ሥራንና ለማህበረሰብ አስተዋጽኦ ማድረግን እንደ ዋና እሴቶቼ ተከትያለሁ።
የመጀመሪያና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን በ_ማክሰኝት ተምሬያለሁ። ከዚያም በሀሮማያዩኒቨርሲቲ በታሪክ ዘርፍ ትምህርቴን በመከታተል ዲግሪ አግኝቻለሁ። ሁለተኛ ድግሪ በባህርዳር ዩንቨርስቲ በትምህርት አመራርና ከሪፍትቫሊ ዩንቨርስቲ በፕሮጀክት ማኔጅመንት ሁለተኛ ዲግራ አግኝቻለሁ
የሥራ ሕይወቴን በ___በመምህርነት፣በትምህርት አመራር ፣በወረዳ አመራር በተለያዩ የስራ ኃላፊነቶች ሰርቻለሁ ላለፉት 16 ዓመታት እንዱሁም የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አባል በመሆን አገልግያለሁ ። በሥራ ዘመኔ የአመራር፣ የአስተዳደር፣ የቡድን ሥራ፣ የችግር አፈታትና የግንኙነት ልምድ አዳብሪያለሁ።
በሥራዬና በማህበራዊ ተሳትፎዬ የተለያዩ ኃላፊነቶችን በመወጣት ለተቋሜና ለማህበረሰቤ የሚችለኝን አስተዋጽኦ አድርጌያለሁ። ከልምዶቼም በመነሳት በተሰጠኝ ኃላፊነት ታማኝነት፣ ትጋትና ኃላፊነት ለመስራት ሁልጊዜ ቅድሚያ እሰጣለሁ።
ወደፊትም ያገኘሁትን እውቀትና ልምድ በመጠቀም ለሀገሬና ለማህበረሰቤ የበለጠ አስተዋጽኦ ማድረግ ዋና ዓላማዬ ነው።