የሕይወት ታሪክ

በ1952 ዓ.ም ከአባቴ መርዳሳ ቱሉና በየሴ ደበሎ ምዕራብ ወለጋ ቂልጡ ካራ ወረዳ ተወለድኩ። ለትምህርት ስደርስ ጎሪ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ገብቼ በ1964 6ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈትኜ ወደ 7ኛ ክፍል አለፍኩ። የ7ኛ ክፍል ትምህርቴን በ1965 ዓም በመንዲ መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማርኩ። በዚሁ ዓመት 7ኛ ክፍል እየተማርኩ የ8ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈትኜ ወደ 9 አለፍኩ። በ1966 9ኛ ክፍል በግምቢ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማርኩ። ከ1967-1969 ነቀምት አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ነበርኩ። ከ1970-1973 መጨረሻ ደርግ አስሮኝ እስር ቤት ነበርኩ። በ1974 አዲስ አበባ ዩኒቬርሲቲ የሶሻል ሳይንስ ኮሌጅ ገብቼ በ1977/1978 የአካዳሚ ዘመን በታሪክ የመጀመሪያ ዲግሪ አገኘውሁ። ከ1978-1981 ቄሌም አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የታሪክ መምህር እና የዘርፉ ክፍል ሃላፊ ሁኜ ሰራሁ። ከ1981 መጨረሻ ጀምሮ በምዕራብ ኦሮሚያ ሲንቀሳቀስ ወደነበረው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ተቀላቀልኩ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በድርጅቱ ወስጥ የተለያዩ ደረጃዎች ላይ ሰርቼሃለሁ። መጀመሪያ በድርጅቱቭየፖለቲካ ትምህርት ቤት የታሪክና የፖለቲካ መምህር በመሆን፡ ቀጥሎ በድርጅቱ የዉጭ ጉዳይ የዲፕሎማሲ ዘርፍ ሃላፊ፡ ከዚያም የድርጅቱ የማስታወቂና የሚዲያ ሃላፊ፡ የድርጅቱ ኮሙኒኬሽን ሃላፊና ቃለ አቀባይ ሁኜቨገልግዬሃለሁ። ከ2014ዓም ጀምሮ በባህልና ስፖርት ሚንስትርነትና ከዚያም በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በሚኒስትር ማዕረግ አማካሪ ሁኜ እያገለገልኩ ነው።